እስስት የእንሽላሊት አይነት ተሳቢ እንስሳ ናት። አንዳንድ የእስስት አይነቶች የቆዳ ቀለማቸውን በመቀያየር ይታወቃሉ። እስስቶች ቀለማቸውን የሚቀይሩበት ምክንያት ሶስት አይነት ሲሆን አንደኛው በአሉበት ስሜት ምክንያት፣ ሁለተኛው በከባቢ ብርሃን፣ እና ሶስተኛው በሙቀት ምክንያት ናቸው። በተለይ የሚገርም ከከባቢ ቀለማት ጋር በመምሰል ለመደብቅ ያለው ችሎታ ነው፤ ከዚህም የተነሣ «እስስታይ» የተባለው አለባበስ በሥራዊቶች ዛሬ ይጠቀማል።
?እስስት | ||||||||||||
---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|
ሳይንሳዊ ደረጃ መስጫ | ||||||||||||
|
እስስቶች ረጅም፣ እሚያታብቅ ምላስ አላቸው። እኒህ ምላሶቻቸው ከሰውነታቸው ሁለት እጥፍ መለጠጥ ይችላሉ። አይኖቻቸው ለየብቻቸው መንቀሳቀስ ይችላሉ። እስስቶች ብዙ ጊዜ ሚመገቡት ትንኞችን ሲሆን አልፎ አልፎ ትናንሽ እንሽላሊቶችን ይበላሉ።
እስስቶች በአውሮጳ፣ አሜሪካና አፍሪካ፣ በተለይም በማዳጋስካር ይገኛሉ።
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article እስስት, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.