አሌ አላሌ

አሌ ሆይ አላሌ ሆይ

ልጆች እግራቸውን ዘርግተው በመደዳ መሬት /ወለል ላይ ይቀመጣሉ። አጫዋች ወይም ከተጫዋቾቹ አንዱ የግር ጠቋሚ ይሆንና በሚዘመረው አንድ ቃል አንድ እግር ይጠቁማል። በመጨረሻው ቃል የሚጠቆመው እግር ይሰበሰብና ከጨዋታ (ከጥቆማ) ውጪ ይሆናል። ጨዋታው እየተደጋገመ ሁለቱም እግሩ የተጠቆመበት (ቁልቢት ያረፈችበት) ልጅ ከጨዋታው ይወጣል። እንዲህ እየተባለ አንድ ልጅ እስኪቀርና አሸናፊ እስኪሆን ጨዋታው ይቀጥላል።

አሌ ሆይ አላሌ ሆይ
ገረዴን አያችሁ ወይ
ገረዴን ማርያም ስማ
በርኩማ አሸክማ
በርኩማ የዳገቴ
የሸማ ቅዳዶቴ
ቀድጄ ቀዳድጄ
ሰጠኋት ላበልጄ
አበልጅ ብትወደኝ
ጨረቃ ሳመችኝ
ጨረቃ ድንቡል ቦቃ
አጤ ቤት ገባች አውቃ
አጤ ቤት ያሉ ልጆች
ፈተጉ ፈታተጉ
በቁልቢት አስቀመጡ
ቁልቢት
ስንዴ ቆሎ
ዳቦ ቆሎ
ይችን ትተሽ
ይቺን አንሺ ቶሎ

አሌሆይ .......... አንድ እግር ይጠቆማል
አላሌሆይ ........ ሁለተኛ እገር ይጠቆማል ..
ገረዴን ..............3ኛ እግር
አያችሁ ወይ ....4ኛ እግር .....እንዲህ እያለ ይቀጥላል

ይችን አንሺ ቶሎ ተብሎ የተጠቆመው እግር ይሰበሰባል፤ የተሰበሰበው እግር ከጨዋታ ውጪ ነው አይጠቆምም።

ጨዋታው ይደገማል ። ጨዋታው ከወጣው እግር ቀጥሎ ባለው እግር እንደገና ይጀምራል ። ሁለቱም እግሮቹ የተጠቆሙበት ከጨዋታ ይወጣል ። ሁሉ ወጥተው አንድ አሸናፊ ልጅ ብቻ እስከሚቀር ይቀጥላል ። ልጆቹ ግጥሙን አውቀው ሁሉም ባንድ ላይ ሲሉት ደማቅ ጨዋታ ይወጣዋል ። አዘማመሩ እንደ « -ግዕዝ ሁ -ካዕብ» አባባል ዜማ ነው

Tags:

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

ጀርመንቢልሃርዝያሞስኮቱርክአዋሳእጸ ፋርስዓፄ ዘርአ ያዕቆብጃፓንማጅራት ገትርአዳም ረታፋይዳ መታወቂያወልቃይትኢየሱስ ጌታ ነውጉልባንጉልበትኢንጅነር ቅጣው እጅጉቤተ ጊዮርጊስሸለምጥማጥሚልኪ ዌይፌጦጠላበጀትፈቃድተረትና ምሳሌ፡ ዳንኤል አበራጳውሎስ ኞኞ«ቅዱስ ሮማዊ መንግሥት»ተውሳከ ግሥኮምፒዩተርታፈሪ ቢንቲይስሐቅቬት ናምአውሮፓስኳር በሽታቅኝ ግዛትክብበእውቀቱ ስዩምጆሮ ጠቢ በሌለበትም ዘንድ ጠብ ጸጥ ይላልየዊኪፔዲያዎች ዝርዝርሃሌሉያቡናኩሻዊ ቋንቋዎችባቲ ቅኝትንጉሥኤሊአብደላ እዝራዩ ቱብአንድምታቤት (ፊደል)አዊጅጅጋአክሱም መንግሥትጃትሮፋጋኔንአውስትራልያእሳት ወይስ አበባአዲስ ኪዳንግራዋሆሣዕና በዓልደጃዝማችየማርክሲዝም ሌኒኒዝም መዝገበ ቃላትጅማየወፍ በሽታባክቴሪያየወታደሮች መዝሙርጌሾሰለሞናዊው ሥርወ-መንግሥትግብፅሚስቱን ገድሎ አማቱ ቤት ተሽሽገአፄፕሮቴስታንትየሥነ፡ልቡና ትምህርትአማርኛየአስተሳሰብ ሕግጋትጋሊልዮሱለይማን እጹብ ድንቅበጅሮንድ🡆 More