1901 ዓ.ም.
1902 ዓ.ም.
- ግንቦት 23 ቀን፦ አራት የብሪታንያ ቅኝ አገሮች አንድላይ ተዋህደው የደቡብ አፍሪካ ኅብረት የተባለ የብሪታንያ ግዛት ሆነ።
- ነሐሴ 16 ቀን፦ ጃፓን ከ1897 ዓም ጀምሮ በጥብቅ ግዛትነት ያስተዳደረችው ኮርያ አገር «በይፋ» ወደ ጃፓን ግዛት ተጨመረ።
1904 ዓ.ም.
1905 ዓ.ም.
- 1920 - ጦርነት የሚከላከል የኬሎግ-ብሪያንድ ውል በ60 አገሮች ተፈረመ።
- - የዓለሙ መጀመርያው ቴሌቪዥን ስርጭት ፈተና ተደረገ።
- 1921 - ሄርበርት ሁቨር የአሜሪካ ፕረዝዳንት ሆነ።
- - የእስቶክ ገበያ ውድቀት በመከሠቱ የመላ አለም ምጣኔ ሀብት ወደ 'ታላቁ ጭፍግግ' በ1 አመት ውስጥ ቶሎ ወረደ።
- 1924 - ጃፓን ማንቹርያን ወረረ።
- 1928 - የሙሶሊኒ ፋሺስታዊ ሠራዊቶች አገራችንን ኢትዮጵያን ወረሩ።
- 1931 - ሂትለርና ስታሊን በሥውር ፊርማ ፖሎኝን አካፈሉ።
- 1932 - ጀርመኖች በ2ኛ ዓለማዊ ጦርነት ለንደንን በቦምብ ለመደብደብ ጀመሩ።
- 1934 - የአላም አል ሓልፋ ውጊያ በጀርመንና እንግሊዝ ታንኮች መኃል በግብፅ በረሃ ጀመረ።
- 1935 - የጓደኞች ወታደርና 1,800 የጣልያ እስረኞች ተሸክማ ላኮኒያ የምትባል መርከብ አፍሪካን ስትቀርብ በጀርመኖች ተተኩሳ ሰጠመች።
- 1936 - ፓሪስ ከተማ በጓደኞች አርበኞች ከጀርመን ነጻ ወጣች።
- 1951 - የቅብጥ አቡና 6ኛ ቂርሎስ ለኢትዮጵያ የራሱን አቡነ እንዲኖሩት ፈቀዱለት።
- 1952 - መጀመርያው ሰው ሰራሽ መንኮራኩር (የሩሲያ) ጨረቃን ደረሰ።
- 1953 - «ኦፐክ» - የዘይት አስወጪ አገሮች ድርጅት - ተመሰረተ።
- 1954 - መጀመርያ ቴሌቪዥን ግንኙነት በአሜሪካና በአውሮጳ መካከል
- 1955 - ዶ/ር ማርቲን ሉጠር ኪንግ «እኔ ሕልም አለኝ» ያለበትን ቃል ለሰላማዊ ሰልፍ ተናገረ።
- 1958 - መጀመርያ የምድር ፎቶ በጨረቃ ምኋር ካለ ሰው ሰራሽ መንኮራኩር ተነሣ።
- 1959 - ጡርጉድ ማርሻል መጀመርያ አፍሪቃ-አሜሪካዊ የዋና ብሔራዊ ችሎት ፈራጅ ተሾሙ።
- 1970 - የጸረ-አፓርትሃይድ ወኪል ስቲቭ ቢኮ በደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ታስሮ ተገደለ።
- 1972 - ነጻነት ለቨንዳ ተሰጠ - ይህ ግን ከደቡብ አፍሪካ ውጭ አልተቀበለም።
- 1975 - የኮሪያ አየር መንገድ አይሮፕላን በሶቭየት ኅብረት ላይ ሲተኮስ 269 መንገደኞች ሞቱ።
- 1978 - በመርዝ ጋዝ አደጋ በካሜሩን 1700 ሰዎች ሞቱ።
- ጳጉሜ 2 ቀን - ዴስሞንድ ቱቱ በኤጲስቆፖሳዊ ቤተክርስቲያን በደቡብ አፍሪካ መጀመርያ ጥቁር ኤጲስ ቆጶስ ሆኑ።
- 1979 - የሬጌ ሙዚቃ ዘፋኝ ፒተር ቶሽ ቤቱ በኪንግስተን ጃማይካ በሌቦች ተገደለ።
- 1981 - ቮየጀር የተባለ ሰው ሰራሽ መንኮራኩር በኔፕቱን ፈልክ አለፈ።
- 1982 - የብረት መጋረጃ በኰሙኒስት ሃንጋሪና በኦስትሪያ መሃል ተከፍቶ ወዲያው ብዙ ሺህ ጀርመኖች ወደ ምእራብ ፈለሱ።
- 1983 - ዑዝበክስታን ነጻነቱን ከሶቭየት ኅብረት አዋጀ።
- 1984 - ፓስካል ሊሱባ በኮንጎ ሪፑብሊክ ምርጫ ፕሬዚዳንት ሆኑ፤ ይህ ምርጫ የረጅም ዘመን አንድ ፓርቲ ግዛት ጨረሰ።
- 1985 - መይ ካሮል ጀሚሶን መጀመርያ ጥቁር አሜሪካዊት በጠፈር ሆነች።
- 1987 - ናቶ በቦስኒያ ሰርቦች ላይ ዘመቻ ጀመረ።
- 1988 - የራፕ ሙዚቃ ተጫዋች ቱፓክ ሻኩር በላስ ቬጋስ ተተኲሶ ተገደለ።
- 1989 - በእስላም ታጣቂዎች በአልጄሪያ በተገረገ እልቂት 60-100 ሰዎች ተገደሉ።
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article 20ኛው ምዕተ ዓመት, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.