አይን የብርሃንን መኖር የሚያሳውቅ የስሜት ህዋስ ነው። ይህንንም ተግባር የሚፈጽመው አሱ ላይ ያረፈውን ብርሃን ወደ ኮርንቲና ኬሚካል በመቀየር ያንን መልእክት በነርቮቻችን አድርጎ ወደ አንጎላችን በማሻገር ነው። ብዙ ህይወት ያላቸው ነገሮች አይን አላቸው ነገር ግን የሁሉም አይን አንድ አይነት ሃይል ወይም ተፈጥሮ የለውም። ለምሳሌ የጥቃቅን እንስሶች አይን እንደሰው ልጅ አይን አካባቢያቸውን በሚገባ ለይተው እንዲያዩ ሳይሆን የሚረዳቸው እንዴው ለወጉ የብርሃንን መኖር ወይም አለመኖር ብቻ እንዲያውቁ ነው የሚረዳቸው። ሌሎች ታላላቅ እንስሳት በጣም የተወሳሰብ አይን ሲኖራቸው አይናቸውም ከአዕምሮአቸው ጋር የሚያያዙባቸው የነርቭ ክፍሎች እንዲሁ የተወሳሰቡ ናቸው። ባጠቃላይ 96% የሚሆን በምድራችን የሚኖሩ እንስሶች የተወሳሰቡ አይኖች ሲኖሩዋቸው እነዚህ የተወሳሰቡ አይኖች በ10 ዓይነት ለይቶ የማየት ችሎታ ይከፈላሉ።
Eye | |
---|---|
የሰው ልጅ አይን. | |
ኮምፓውንድ አይን የአንታርክቲ ቅሪል |
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article አይን (ሥነ አካል), which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.