ዓመተ ምሕረት ከኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ አለም መምጣት ጋር ተያይዞ በአብዘኛው ክርስቲያናዊ ማሕበረሰብ ዘንድ ለዘመን መግለጫነት ወይም መጠሪያነት የሚሰጥ ስያሜ ነው።
በመካከለኛው ዘመን ላቲንኛ ዐኖ ዶምኒ (AD) ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ትርጓሜው ዘመነ ጌታ ወይም የጌታችን ዘመን የሚል ነው፤ ይህም የተወሰደው "ዐኒ ዶምኒ ኖስትሪ ጄሱ ክርስቲ" (በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ዘመን) ከተሰኘ ላቲን ኃይለ ቃል ነው። በኢትዮጵያም ለዚሁ በቀረበ መልኩ ዓመተ ምሕረት በመባል ተተርጉሟል። አንዳንድ ጊዜ ሰኩለር ለማድረግ ስፈልጉ የተለያዩ ፀሐፍት ከ፲፯ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መባቻ ጀምሮ የጋራ ዘመን ወይም ኮሜን ኢራ(ሲ.ኢ) በማለት የመጻፍ የጀመሩ ቢሆንም እንደምክንያትነት የሚወሰደው ነገር የኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር መምጣት እንድሆነ ይታምናል።
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ዓ.ም., which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.