ቡዲስም

ቡዲስም በጎታማ ቡዳ ትምህርቶች የተመሠረተ እምነት ነው። ይህም በ፮ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ.

የኖረ የሕንድ አገር መስፍን ነበረ። ቡዲስም በካምቦዲያ እና በቡታን በይፋ የመንግሥት ሃይማኖት ነው።

ቡዲስም
ጎታማ ቡዳ ሃይማኖቱን ሲያስተምር

የቡዲስም መጀመርያ እንደ አንድ የሕንድ አገር ፍልስፍና ነበረ። በጎታማ ትምህርት የጽድቅ ኑሮ የሚይዙ ሰዎች ወደ ከፍተኛ ደረጃ ደርሰው ከሰምሳረ ወይም ከተመላሽ-ትስብዕት ማምለጥ፣ ከሕልውና ወደ «ኒርቫና» (ኢ-ሕልውና) ማምለጥ የሚፈለግ ዒላማ ነው። ስለ አምላክ ወይም ስለ እግዚአብሔር ግን አያስተምርም፤ ከፍተኛ ደረጃ የደረሱት እንደ ጎታማ ቡዳ አማልክቱ ወይም «ቡዳዎች» ይባላሉ። ለቡዳዎችም ምስል ተቀርጾ መሥራትና የምስሎች አምልኮት እንደ አብርሃማዊ ሃይማኖቶች (አስርቱ ቃላት) ኃጢአት ሳይባል፣ እንደ ጽድቅ ይቆጠራል፤ ይህም ልማድ የተገኘው በባክትሪያ (አፍጋኒስታን) ከታላቁ እስክንድር ዘመቻ ጀምሮ ከኖሩት ግሪክ-ቡዲስቶች ነበር። በዚህ ዓለም ሀዘን ከደስታ ጋር ሲፈራረቅ ለመንፈስ ወይም ነፍስ ሕልውና ባለውለታ በመሆን ፈንታ፣ ነፍስ የሚባለው ወይም ነጻ ፈቃድ ምታቶች ናቸው ይላሉ።

ከነዚህ ልዩነቶች በቀር፣ በተለይ ከአስርቱ ቃላት መጀመርያ 4 ቃላት ቢለዩም፣ በተረፈ ግን በአጠቃላይ ከመጨረሾች 6 ቃላት ጋር ይስማማሉ። በተለይም፦

  • «የባልንጀራህን ሀብት አትመኝ» - በቡዲስም ዘንድ ደግሞ መመኘትን ሁሉ ማጥፋት፣ እንዲሁም ገዳም ገብቶ መኖኩሴ መሆን እንደ ጽድቅ ነው።
  • «እናትህንና አባትህን አክበር» - በቡዲስም ደግሞ ቁም ነገር ነው፤ እንዲሁም ለችግረኞች ምጽዋትና ልግሥና ማድረግ ጽድቅ ነው።

ቡዲስም በእስያ አገራት ተስፋፍቶ ሁለት ዋና ክፍሎቹ ጤራቫዳ ቡዲስምና ማሃያና ቡዲስም ይባላሉ። በጤራቫዳ ቡዲስም ዘንድ፣ ሳንስክሪትና ፓሊኛ እንደ ተቀደሱ ቋንቋዎች ይቆጠራሉ።

ፓሊኛ በተለይ ለቡዲስም ፍልስፍና ጽሑፎች ለመጻፍ ከሳንስክሪት የተደረጀው የልጆች ቋንቋ ይመስላል፤ ስለዚህ እንደ ሳንስክሪት የሕንዳዊ-አውሮፓዊ ቋንቋዎች ቤተሠብ አባል ነው። የፓሊኛ ሕንዳዊ-አውሮፓዊ ቃላት ድምጽ ወደ «ኒርቫና» ደረጃ እንደሚመራ ያምናሉ።

በቡዲዝም እምነት አስተምሮት መሠረት ፈጣሪ ሚባለውን አካል ከውስጥ መፈለግ እና በሁሉም ነገር ሊተካ የሚችል ነው!!

:

Tags:

ሕንድቡታንካምቦዲያየመንግሥት ሃይማኖትጎታማ ቡዳ

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

የወንዶች ጉዳይዚምባብዌስሜን አፍሪካየኢትዮጵያ ሕግሐረሪ ሕዝብ ክልልግዕዝ አጻጻፍንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያቀዳማዊ ዓፄ ዮሐንስፕላኔትውሻአርባ ምንጭየሰው ልጅ ጥናትሰጎንሥነ ጥበብሰዓሊየኦሎምፒክ ጨዋታዎችደመቀ መኮንንሥርዓተ ነጥቦችኔቶቢራበእንግሊዝ የሚገኙ የእግር ኳስ ሜዳዎች ዝርዝርአዲስ ዘመን (ጋዜጣ)ቅዱስ ገብረክርስቶስየተባበሩት ግዛቶችደበበ ሰይፉአስናቀች ወርቁወደፊት ገስግሺ ውድ እናት ኢትዮጵያሰሜን ተራራየልብ ሰንኮፍየዔድን ገነትራስ ዳርጌየመንግሥት ሃይማኖትመንፈስ ቅዱስፔንስልቫኒያ ጀርመንኛትዝታመጽሐፈ ጦቢትደራርቱ ቱሉከበደ ሚካኤልኦሪት ዘፍጥረትጳውሎስ ኞኞኦሮሞማሲንቆየመጀመሪያው የዓለም ጦርነትሚዳቋፖለቲካየቅድስት ድንግል ማርያም ስሞችሻማዋናው ገጽ/ለጀማሪወች/ፊደል አጻጻፍየቀዳማዊ ዓፄ ዮሐንስ ዜና መዋዕልቁስ አካልሼክስፒርናዚ ጀርመንየሒሳብ ምልክቶችየኢትዮጵያ ሙዚቃየኢትዮጵያ አየር መንገድቻይንኛባሻየድመት አስተኔእሪያክርስትናሂሩት በቀለ19ኛው ክፍለ ዘመን የግራኝና የልብነ ድንግል ታሪክ በአማርኛፋርስየጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበርኤስቶንኛLቁልቋልውሃMአክሱም መንግሥትዋና ከተማኦሮማይአሕጉርየኢትዮጵያ የ5 ሺ ዓመት ታሪክ ከኖኅ እስከ ኢህአዴግፈሊጣዊ አነጋገር ደ🡆 More