መዝገበ ዕውቀት (ኢንሳይክሎፒዲያ) ማለት ወይም የዕውቀት ዘርፎች ሁሉ ወይም የአንድ ዕውቀት ዘርፍ የመረጃ ክምችት ነው። ከመዝገበ ቃላት የሚለይበት ጥቅሙ እያንዳንዱ መጣጥፍ ስለ አንድ ቃል ወይም ዘይቤ ብቻ ሳይሆን ጥልቀት ያለው መረጃ እሚሰጥ መሆኑ ነው። ስለዚህ የመዝገበ ዕውቀት መጣጥፍ ከመዝገበ ቃላት መጣጥፍ ይልቅ ረጅምና ዝርዝሩን የሚገልጽ ነው። ከሁሉ ጥንታዊው እስካሁንም የሚገኘው መዝገበ ዕውቀት የፕሊኒ መጽሐፍ ናቱራሊስ ሂስቶሪያ ወይም «የተፈጥሮ ታሪክ» (69 ዓ.ም.
በሮማይስጥ ተጽፎ) ይባላል። በአሁኑ ዘመን በኢንተርኔት የሚነቡ ብዙ መዛግብተ ዕውቀት (ለምሳሌ ውክፔዲያ) ሊገኙ ይቻላል።
ዕውቀት የተሳተ መረጃ ሊሆን እንደሚችል ሁሉ፣ መዝገበ ዕውቀት «መዝገበ ዕውነት» ከቶ አይሆንም። ለመሆኑ ግን በዞራስተር ጽሑፍ መሠረት «መዝገበ ዕውነት» (ሃታ-ማራኒሽ) የእግዚአብሔር 16ኛው ስያሜ ነው።
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article መዝገበ ዕውቀት, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.