ፋሲካ

ፋሲካ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን መካከል የተነሳበትን የትንሳዔ ቀን ማሰብያ ዕለት ነው።

ስሙ ፋሲካ የመጣው ከአረማይክ /ፓስኻ/፣ ግሪክኛ /ፓስቃ/፣ ዕብራይስጥ /ፐሳኽ/ ሲሆን፤ የአይሁድ ፋሲካ በዓል ዕብራውያን በሙሴ መሪነት ከግብፅ ፈርዖን ግዛት በተዓምራትና በመቅሠፍቶች የወጡበትን ጊዜ ለማክበር ነበር። ይህ ታሪክ በተለይ በብሉይ ኪዳን ኦሪት ዘጸአት ይገለጻል። በተለይ በዘጸአት 12፡23 በአሥረኛው መቅሠፍት ጊዜ "እግዚአብሔር ያልፋል" ሲል፥ "ያልፋል" የሚለው ግሥ በዕብራይስጡ /ፐሳኽ/ ስለ ሆነ፣ ስሙ ፋሲካ ከዚያው ቃል ደረሰ።

አዲስ ኪዳን ዘንድ ደግሞ ኢየሱስ ለፋሲካ በዓል አዲስ ትርጉም ሰጠው። በመጨረሻው እራት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር የበዓሉን ዝግጅት ሲጠብቅ ሥጋ ወደሙ እንደ መስዋዕቱ ሆኖ ባካፈለው ኅብስትና ወይን በኩል እንደሚገኝ አመለከተ። ኢየሱስም ተሰቅሎ ከ፫ ቀን በኋላ ተነስቶ ዳግመኛ ለደቀመዛሙርቱ ታይቶ፣ በነዚህ ዘመኖች ፍፃሜ ለፍርድ ቀን በሕያዋንና በሙታን ለመፍረድ እንደሚመለስ ነገራቸው። ይህ ሁሉ አሁን በክርስትና ወይም በአብያተ ክርስቲያናት በፋሲካ በዓል የሚከበር ነው። በፋሲካ በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳም የገባለትን ቃል ኪዳን፤ ማለትም ከልጅ ልጅህ ተወልጄ ስጋዬን ቆርሼ ደሜን አፍስሼ አድንሀለሁ ባለው ቃል መሰረት፤ ወደዚህ አለም ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ሰው ሆኖ አዳምን ከሰይጣን አገዛዝ ነጻ ሊያወጣው፤ የአዳምን በደል እርሱ ሊክስ የተሰቀለበት ጊዜ ይታሰብበታል።

በፋሲካ ከሚደረጉ ነገሮች አሉ።

Tags:

ትንሳዔኢየሱስ ክርስቶስ

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

የአለም አገራት ዝርዝርተረትና ምሳሌደሴቅልልቦሽተክለ ሐዋርያት ተክለ ማርያም (ፊታውራሪ )ሐና ወኢያቄምጋብቻመዝሙረ ዳዊትአውሮፕላንመንግሥቱ ንዋይባሕር-ዳርሥላሴየኮንሶ ባህላዊ የእርከን ስራ1 ሳባየኢትዮጵያ ሕገ መንግስትየኖህ መርከብየአገሮች ገንዘብ ምንዛሪዶሮየኢትዮጵያ ሙዚቃኒንተንዶባሕላዊ መድኃኒትውዳሴ ማርያምደጃዝማችየባቢሎን ግንብግራኝ አህመድጄኖቫንብቫስኮ ደጋማአባይ ወንዝ (ናይል)ሐረግ (ስዋሰው)አስቴር አወቀካይ ሃቨርትዝራስ መኮንንቻይናለጀማሪወች/አርትዖኤፍሬም ታምሩየጣልያን ታሪክየሰው ልጅ ጥናትግዕዝእግር ኳስስፖርትቀይ ተኩላቱርክየወላይታ ዞንየኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ መሣሪያዎችቺኑዋ አቼቤየኢትዮጵያ ብሔራዊ ፓርክአክሱም መንግሥትመብረቅደርግአለቃ ገብረሐና እና አስቂኝ ቀልዶቻቸውምሥራቅ አፍሪካወንጀለኛው ዳኛፌስቡክዓፄ ሱሰኒዮስወጋየሁ ደግነቱዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግአፈወርቅ ተክሌህብስት ጥሩነህሥራመንፈስ ቅዱስሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃትግራይ ክልልፖለቲካቅዱስ ገብረክርስቶስፍትሐ ነገሥትመጽሐፈ ጦቢትፈቃድየቢራቢሮ ክፍለመደብሥነ ጽሑፍቅዱስ ላሊበላአምልኮ🡆 More