ቤኒን: በምዕራብ አፍሪካ ውስጥ ሉዓላዊ መንግስት

ቤኒን ወይም በይፋ የቤኒን ሪፐብሊክ በምዕራብ አፍሪካ የምትገኝ ሀገር ናት። ከምዕራብ ቶጎን፣ ከምሥራቅ ናይጄሪያን እና ከሰሜን ቡርኪና ፋሶና ኒጄርን ትዋሰናለች። ዋና ከተማዋ ፖርቶ ኖቮ ሲሆን የመንግሥቷ መቀመጫ ግን ኮቶኑ ከተማ ናት። የቤኒን የቆዳ ስፋት ወደ 110,000 ካሬ ኪ.ሜ.

ሲሆን የሕዝቧ ብዛት ደግሞ ወደ 9.05 ሚሊዮን ይገመታል።

République du Bénin
የቤኒን ሪፐብሊክ

የቤኒን ሰንደቅ ዓላማ የቤኒን አርማ
ሰንደቅ ዓላማ አርማ
ብሔራዊ መዝሙር L'Aube Nouvelle

የቤኒንመገኛ
የቤኒንመገኛ
ቤኒን በቀይ ቀለም
ዋና ከተማ ፖርቶ ኖቮ፣ ኮቶኑ
ብሔራዊ ቋንቋዎች ፈረንሳይኛ
መንግሥት
ፕሬዝዳንት
የብዙ ፓርቲ ዴሞክራሲ
ፓትሪስ ታሎን
ዋና ቀናት
ሐምሌ ፳፭ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ.ም.
(August 1, 1960 እ.ኤ.አ.)
 
ነጻነት ከፈረንሳይ
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
ውሀ (%)
 
114,763 (100ኛ)

0.4
የሕዝብ ብዛት
የ2016 እ.ኤ.አ. ግምት
የ2013 እ.ኤ.አ. ቆጠራ
 
10,653,654 (84ኛ)

10,008,749
ገንዘብ ምዕራብ አፍሪካዊ CFA ፍራንክ
ሰዓት ክልል UTC +1
የስልክ መግቢያ +229
ከፍተኛ ደረጃ ከባቢ .bj

የቤኒን ይፋ ቋንቋ ፈረንሳይኛ ሲሆን እንደ ፎንና ዮሩባ የመሳሰሉት የሀገሪቷ ባህላዊ ቋንቋዎች ሰፊ ተናጋሪ አላቸው። የሮማ ካቶሊክ ክርስትና ብዙ ተከታዮች ሲኖሩት እስላሞች፣ ፕሮቴስታኖችና የቩዱ ተከታዮችም ይገኛሉ። ቤኒን የተባበሩት መንግሥታት፣ የአፍሪካ ሕብረት እናም ሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች አባል ናት።

ከ17ኛው እስከ 19ኛው ክፍለ ዘመን እ.ኤ.አ. የሀገሪቱ መሬት በዳሆሚ መንግሥት ነበር የሚመራው። በ17ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ የአትላንቲክ የባሪያ ንግድ በአካባቢው ሰፍቶ ስለነበር ቦታው የባሪያ ጠረፍ ይባል ነበር። በ1892 እ.ኤ.አ. ፈረንሳይ አካባቢውን በመቆጣጠር የፈረንሳይ ዳሆሚ ብላ ሰየመችው። በ1960 እ.ኤ.አ. ዳሆሚ ነፃነቷን በማግኘት ለ፲፪ ዓመታት በዴሞክራሲያዊ መንግሥት ተመርታለች።

ከ1972 እስከ 1990 እ.ኤ.አ. ሀገሪቷ በማርክሲስት ሌኒኒስት አቋም የቤኒን ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ተብላ ተሰመች። በዚህ ጊዜ በሀገሪቷ የኢኮኖሚ ውድቀት ተከስቶ ነበር። በ1991 እ.ኤ.አ. የቤኒን ሪፐብሊክ ተመሠረተ።

ቤኒን ወደ ውጭ የሚልከው ዋንኛ ምርት ጥጥ ሲሆን ከዚህ በላይ ካሸው ለውዝ (Anacardium occidentale)፣ ኮኮነት፣ ዓሳ፣ እንጨት ወደ ውጭ ይላካሉ። ፔትሮሊየምና ወርቅም ይላካሉ። ባለፉት ዓመታት ውስጥ ቤኒን ለተግባራዊ ሳይንስ ምርመራ ጥናት አንጋፋ ማዕከል ሆናለች።

በደቡብ ቤኒን ባሕላዊ አበሳሰል፣ በተለይ የበቆሎ ዳቦ በኦቾሎኒ ወጥ ወይም በቲማቲም ወጥ ይጠቀማል። አሳ እና ዶሮ ከሁሉ ተራ ሥጋዎች ናቸው፣ በሬ፣ ፍየልና የጫካ አይጥ ደግሞ ይበላሉ። በስሜን ቤኒን ባሕላዊ አበሳሰል፣ በተለይ ኮቴሃሬ በበቆሎው ፈንታ ይጠቀማል። ቤሬ ወይም አሳማ በጥብስ ወይም በወጣወጥ፣ ፎርማጆ፣ ኩስኩስ፣ ሩዝ፣ ባቄላ፣ ፍራፍሬ በሰፊው ይጠቀማሉ።

እግር ኳስ ከሁሉ የሚወድ እስፖርት ሲሆን፣ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ቤስቦል ወደ ቤኒን ገብቷል።

ማጣቀሻ

ቤኒን: በምዕራብ አፍሪካ ውስጥ ሉዓላዊ መንግስት 
በ"Wiki Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለ ቤኒን የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።


Tags:

ምዕራብ አፍሪካቡርኪና ፋሶቶጎኒጄርናይጄሪያፖርቶ ኖቮ

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

ፅጌ ማርያም ገብሩ ደስታአማርኛ ልብ ወለድ መፃህፍትአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስማሞ ውድነህሽኮኮዓፄ ዘርአ ያዕቆብራስአላማጣሐረሪ ሕዝብ ክልልየአፍሪቃ አገሮችምሳሌይምርሃነ ክርስቶስጥቁር እንጨትሙርሌኛዮሐንስ ፬ኛኣዞ ሓረግጋስጫ አባ ጊዮርጊስ2 ናቡከደነጾርመንግስቱ ለማማህበራዊ ሚዲያከአባእጸ ፋርስሳን ሆዜ፣ ካሊፎርኒያዳግማዊ ዓፄ ኢያሱአብዲሳ አጋግንቦትአባ ሊቃኖስእንግሊዝኛሀጫሉሁንዴሳቤተ እስራኤልንዋይ ደበበሱፍቶማስ ኤዲሶንየአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃ ቤትበጅሮንድዲየጎ ማራዶናኦሮሞወፍየኮርያ ጦርነትጂራንየእንግሊዝ ወሽመጥሊዮኔል ሜሲድብርትጣይቱ ብጡልባህር ዛፍየደጋ አጋዘንመሀመድ ሁሴን አሊ አላሙዲሉዊስ አልቤርቶ ሱዋሬዝየዓለም፡ታሪክ፡ከፍጥረት፡ጀምሮ፡እስከ፡ዘመናችን፡ድረስ፡ 1834ሳዑዲ አረቢያየፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽንሊዮናርዶ ዳቬንቺድረ ገጽገዳዩ ባልሽ የሞተው ወንድምሽጨረርጦጣየማቴዎስ ወንጌልሰይጣንታሪክፊታውራሪክርስቶስ ሠምራመንግስቱ ኃይለ ማርያምዳማ ከሴአሚር ኑር ሙጃሂድናይሎ ሳህራዊ ቋንቋዎችማርክሲስም-ሌኒኒስምመጽሐፈ ሲራክልጅየኢትዮጵያ ታሪክ፡ ሐሪ አትከንስኮሶ በሽታአዶልፍ ሂትለርመስቃንዓረፍተ-ነገርስም (ሰዋስው)ቆለጥወይን ጠጅ (ቀለም)🡆 More