J / j በላቲን አልፋቤት ፲ኛው ፊደል ነው።
የላቲን አልፋቤት | ||||||
---|---|---|---|---|---|---|
A | B | C | D | E | F | |
G | H | I | J | K | L | M |
N | O | P | Q | R | S | T |
U | V | W | X | Y | Z | |
ተጨማሪ ምልክቶች፦ | ||||||
Þ... |
ከ1516 አስቀድሞ፣ የላቲን ፊደል I ለተነባቢው «ይ»፣ ለአናባቢው «ኢ»፣ እና ለሮማይስጡ ቁጥር ፩ ተጠቀመ። ሆኖም በቃል መጨረሻ ሲደረብ እንደ -ii ሲጻፍ፣ ቅርጹ እንደ -ij ይምሰል ጀመር። ከ1516 ዓ.ም. ጀምሮ ቅርጹ «J» ለተናባቢው «ይ» እና ቅርጹ «I» ለአናባቢው «ኢ» ይለያዩ ጀመር።
በፈረንሳይኛ ግን የ«ይ» ድምጽ አጠራር ከዚያ በፊት እንደ «ጅ» ለመምሰል ስለ ጀመረ፣ እሱ ደግሞ በጥንታዊ ፈረንሳይኛና እንዲሁም በእንግሊዝኛ በ«I» ይጻፍ ነበር፣ ከ1625 ዓም ጀምሮ ግን በ«J» ይጻፍ ጀመር። እስካሁንም ድረስ «J» በእንግሊዝኛ እንደ «ጅ» ያሰማል፤ በፈረንሳይኛ ድምጹ እንደገና ተለውጦ አሁን እንደ «ዥ» ያሰማል። በዘመናዊ እስፓንኛ ግን J እንደ «ሕ» ያሰማል።
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article J, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.