እግዚአብሔር የግዕዝ ቋንቋ ቃል ሲሆን ትርጓሜውም እግዚእ ማለት ገዢ ወይም ጌታ ሲሆን፤ ብሔር ማለት ደግሞ ስብሰባ /ብሄር ወይም አገር ማለት ነው። የተሟላ ትርጉም ፡ የብሔር ገዢ ከሁሉ በላይ የሆነ ፡ ዓለምን የፈጠረ ፡ ብቸኛ አለቃ ማለት ነው።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የተጻፉት በሶስት ቋንቋዎች ሲሆን የመጀመሪያው ክፍል በዕብራይስጥና በአረማይክ እንዲሁም የኋለኛው በግሪክ መሆኑ ይታወቃል። እግዚአብሔር በሚለው የግዕዝ ቃል የተተካው ስም በዋነኞቹ እና በመጀመሪያዎቹ ቅጅዎች የፈጣሪን ስም የሚወክሉት አራት የእብራይስጥ ፊደላት (יהוה) ተጽፎ የነበረ ሲሆን አጠራራቸውም ዮድ ሄ ዋው ሄ ነው። በቀድሞ ዘመን ተነባቢዎች ብቻ የሚጻፉ ሲሆን አናባቢዎችን የሚጨምረው አንባቢው በመሆኑ በዘመናችን የእነዚህን አራት ፊደላት ትክክለኛ አነባበብ በእርግጠኛነት የሚያውቅ የለም። ሆኖም ወደ ትክክለኛው በእጅጉ የሚቀርቡ ሁለት የአማርኛ አጠራሮች ይገኛሉ። እነሱም ይሖዋ እና ያህዌህ የሚሉት ሲሆኑ በ1879 የአማርኛ ትርጉም መፅሓፍ ቅዱስ አንድ ጊዜ (ይሆዋ)፣ በ1941 ትርጉም ሁለት ጊዜ (ያህዌ) አንዲሁም በአዲሱ መደበኛ ትርጉም እጅግ በርካታ ቦታ ላይ (ያህዌ) በሚል ተጽፈው ይገኛሉ።
በግዕዝ ፍልስፍና B-H-R (𐩧𐩢𐩨) የሚለው ሥር ብሔር ወይም ባሕር ከመስጠት በላይ ትርጉሙ ማናቸውም ባሕር ዓይነት፣ የዓለም፣ የሀሣብ፣ የድምጽ፣ የጠፈር፣ ወይም የመንፈስ ባሕር ቢሆን፤ ባሕሩ የባሕሩም ክፍሎች ሁሉ ወሰኖች እንዳሉባቸው በቀላል ሊገለጽ የሚችል ነው። እንግዲህ ወሰኖቹን የሚወስነው አወሳኝ ወይም ገዢው ኃይል «ብሔሩን የሚገዛ» ወይም በግዕዝ «እግዚአብሔር» በመባል ሊታወቅ ይቻላል። ይህ ላይኛ ፈቃድ ፈጣሪው ጸባይ የሰማዩ አባታችን ሲሆን ያለ እርሱ ረድኤት ምንም አለመቻሉን የሚል ግንዛቤ ነው። ስለዚህ የማናቸውም ተቃዋሚ ወይም ጋኔን ፈቃድ ቢኖር በእግዚአብሔር ፈቃድና ትግዕስት ብቻ ነው ስንኳ ለጊዜው ሊቃወሙት የሚቻለው (ኩፋሌ 10:5-7)።
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article እግዚአብሔር, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.