ሮቃ

ሆማር፣ ሆመር፣ ወይም እንደ ኦሮምኛ ሮቃ (Tamarindus indica) ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ዛፍ ተክል ነው።

ሮቃ
ሆማር / ሮቃ
ሮቃ

የተክሉ ሳይንሳዊ ጸባይ

እስከ 15 m. የሚደርስ ሁሌ ለም ነው።

ፍሬው በውስጡ ዘሮቹ አሉት።

አስተዳደግ

ዘሮቹ ጉንቆል ለማድረግ ለአጭር ጊዜ ሊፈሉ ይቻላል። ከዚያ ደረቅ ቢቆዩ ለጥቂት ወሮችም ረቢ ይሆናሉ።

ዛፉ ረጅም ሕይወት አለው፣ በ3 ወይም 4 አመት ውስጥ ያፈራል።

ፍሬው ቡናማ ወይም ቀይ-ቡናማ ሲሆን ይመረታል። አንድ ዛፍ ብቻ በየዓመቱ 1.75 ኩንታል ፍሬ ሊሰጥ ይችላል።

በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድር

በእርጥብ ቆላ ደኖች፣ በወንዝ ዳሮች፣ በጉንዳን ጎጆች መኃል፣ ከ 800-1600 m ከፍታ ይገኛል።

በአፍሪካና በየመን በዱር ኗሪ ተገኝቷል፣ በተረፈውም አለም ተለምዷል።

የተክሉ ጥቅም

በተለይ በሕንድ በሌሎችም አገራት እንደ ሰብለ ገበያ ይታደጋል።

ፍሬው ጥሬ ሲሆን ደግሞ ይበላል። ፍሬው በአለም ዙሪያ በብዙ አይነት ጣፋጭ አበሳሰል ውስጥ ይገኛል። በላቲን አሜሪካ አንድ መጠት «ታማሪንዶ» ከተፈላው ፍሬ ይሠራል።

ፍሬውም እንደ አቀዝቃዥ፣ ምግብ ፈጪ፣ በሆድ መነፋት ላይ፣ ለሚያስቀምጥ መድሃኒት፣ በእስኩርቪም ላይ ይጠቀማል።

ፍሬው ከሞከከ ስለ አሲዱ መዳብንም ሆነ ነሐስን ለማጽዳት ይስማማል።

በሎሚ ጭማቂ ፈንታ የሆማር ጭማቂ ቅዝቃዛ መጠት ይሆናል። በአስመራ የደረቀው ፍሬ እና ጭማቂው በሱቅ ተገኝተው ነበር።

እንጨቱ ለከሰል ማለፊያ ነው።

ቅጠሎቹ ከፍ ያለ አሲድ አለባቸው፣ በብጉንጅ ላይ እንደ አምቅ ያገልግላሉ። የውስጡ ዘሮቹም በተቅማጥ ተጠቅመዋል።

ዘይቶቹ በአየሩ ተናኝ ስለሆኑ፣ በዛፉ ጥላ መቀመጥ የሚያረጋ ውጤት እንዳለው ተዘግቧል።

በሌሎችም አገራት ፍሬው ለሆድ ድርቆት እንደሚያስቀምጥ መድሃኒት ታውቋል።.

በደቡብ-ምሥራቅ እሥያ፣ የቅጠሉም አምቅ በግንባሩ ለትኩሳት ማከሙ ይታወቃል።

በናይጄሪያ በተደረገ 1998 ዓም ጥናት፣ ሆማር ፀረ-ባክቴሪያ ባህሪዮች እንዳሉት ተረጋገጠ።

Tags:

ሮቃ የተክሉ ሳይንሳዊ ጸባይሮቃ አስተዳደግሮቃ በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድርሮቃ የተክሉ ጥቅምሮቃኢትዮጵያኦሮምኛ

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

ቴሌቪዥንአሊ ቢራአዲስ አበባነጠላ ጫማቤተክርስቲያንማኅበረ ቅዱሳንታሪክ ዘኦሮሞአማርኛ ልብ ወለድ መፃህፍትጁፒተርየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየኖህ መርከብቡዳአቡነ አረጋዊ ዘደብረ ዳሞደመናየዓለም ዋንጫኦሪት ዘፍጥረትሶፍ-ዑመርጡት አጥቢመሬትፍርድ ቤትጋን በጠጠር ይደገፋልከባቢ አየርደራርቱ ቱሉአስረካቢቀዳማዊ ቴዎድሮስመዝገበ፡ቃላት፡በአምኅርኛ።አዋሽ ወንዝሐምሌመጥምቁ ዮሐንስአርሰናል የእግር ኳስ ክለብፖለቲካኢትዮ ቴሌኮምአቶምአክሊሉ ሀብተ-ወልድፈሊጣዊ አነጋገር መክሬዲት ካርድፈሊጣዊ አነጋገር ሀብሉይ ኪዳንቡላደመቀ መኮንንየአሜሪካ ፕሬዚዳንትኡራኑስቼክአላህአውግስጦስእንጀራአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ19ኛው ክፍለ ዘመን የግራኝና የልብነ ድንግል ታሪክ በአማርኛAፈሊጣዊ አነጋገር የየኦሮሞ ዘመን አቆጣጠርአንዶራሩዋንዳጭፈራድንገተኛስም (ሰዋስው)የግሪክ አልፋቤትየማቴዎስ ወንጌልየኢትዮጵያ ቋንቋዎችቁርአንድንቅ ነሽደብረ ታቦር (ከተማ)የኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ መሣሪያዎችየትነበርሽ ንጉሴመዝገበ ቃላትመናፍቅቅድመ-ታሪክዛይሴጂጂየኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማፈንገስሄክታርጸጋዬ ገብረ መድህንገደብኩናማ🡆 More