ጳውሎስ ኞኞ

ደራሲ ጳውሎስ ኞኞ ኅዳር 11 ቀን 1926 ዓ.ም ቁልቢ አካባቢ ተወለደው ድሬዳዋ ከተማ አደጉ። በጣሊያን ወረራ ምክንያት ትምህርታቸውን ከ4ኛ ክፍል በላይ ለመቀጠል አልቻሉም ነበር። ብልህ አዕምሮና የፈጠራ ችሎታ የነበራቸው ሰው ስለነበሩ፤ በልጅነታችው የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ጣሊያንን ሲገድሉ ወይንም ሲማርኩ ሥዕል በመሣል ያሳዩ ነበር። ጳውሎስ ካላቸው የጽሑፍ ጥማት የተነሳ የ«ድምጽ ጋዜጣ» አዘጋጅ በመሆን የብዕር ድምጻቸውን ያሰሙ ነበር። ጋዜጦች ላይ ከጽሑፍ አቅራቢነት እስከ አዘጋጅነት ለበርካታ ዓመታት ሠርተዋል። በተለይ «አንድ ጥያቄ አለኝ» በሚለው የአዲስ ዘመን ጋዜጣ አምዳቸው ላይ ብዙ ታዋቂነትን አግኝተዋል። አቶ ጳውሎስ ኞኞ ከ1955 ዓ.ም ጀምሮ ለኢትዮጵያ ስነ ጽሑፍ ዕድገት የነበራቸውን ተሰጥኦ በአግባቡ በሥራ ላይ ያዋሉ እውቅ ጋዜጠኛና ደራሲ ነበሩ። እኚህ ታዋቂ ሰው በተወለዱ በ58 ዓመታቸው ሞቱ።

ጳውሎስ ኞኞ
ጳውሎስ ኞኞ (በስተግራ)
ጳውሎስ ኞኞ
አቶ ጳውሎስ ኞኞ

አቶ ጳውሎስ የጌታችው ሚስቶች በሚል ርዕስ ያሳተሟትን መጽሐፍ፤ «ከታተመችበት ወር አንሥቶ ላንድ ዓመት የመጽሐፌ መብት የግሌ ነው፡ ከአንድ ዓመት በኋል መብቱ የማንኛውም ኢትዮጵያዊ ይሁን፡ ከወሰንኩት ጊዜ በኋላ አሳትሞ ለመሸጥ የፈለገ ሁሉ ከድርሰቴ ሳይቀንስም ሆነ ሳይጨምር ሊያራባው ይችላል። ስሜን ሳይሰርዝ 'አሳታሚውን እገሌ' ብሎ ማንም ኢትዮጵያዊ ከፈለገ እንዲያራባት የደራሲነት መብቴን ልቅቄአለሁ፡ አሳታሚው የግሉን የመግቢያ ሐተታ በስሙ ቢጽፍ እኔም ሆንኩ ወራሼ አንቃወምም።» ብለዋል

የጳውሎስ ኞኞ ድርሰቶች

ከጋዜጠኝነታቸው ጎን ለጎን በድርሰትና በታሪክ ጸሐፊነታቸውም ፲፱ መጻሕፍት የታተመላቸው ሲሆን ሁለቱ ካረፉ በኋላ የታተሙ ናቸ። ለሕዝብ የሚሆኑ ዕውቀት ተኮር መጻሕፍት በማቅረብ ይታወቁ የነበሩት አቶ ጳውሎስ ኞኞ ካረፉ ከ፳ ዓመታት በኋላ ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ በሀገር ውስጥ የተጻጻፏቸውንና ወደውጭ አገር የላኳቸውን ደብዳቤዎች የሚያሳዩት ሁለት መጻሕፍት በአስቴር ነጋ አሳታሚ ድርጅት አማካይነት ታትመዋል።

አጫጭር ልብ ወለዶች

  • ከሴቶቹ አምባ
  • የአራዳው ታደሰ
  • የጌታቸው ሚስቶች
  • ድብልቅልቅ
  • የኔዎቹ ገረዶች

ታሪካዊ መጻሕፍት

ጥቅስ

ስለጸሐፊነት ባህሪያቸው ሲጽፉ፦ «'ይምሰል አይምሰል የጠይብ እጅ ከከሰል' እንደሚባለው እጄ እንደልማድ ሆኖበት መሞጫጨርን ይወዳል፡ ያን ሟጫራዬን ደግሜ ካነበብኩ ቀድጄ መጣል ነው፤ ይሰለቸኛል፡ እጠለዋለሁ፡ ስለዚህ አንድ ጊዜ በማርቀቅ የጻፍኳትን እንድትታተም እፈርድባታለሁ። ምናልባት አባጣ ጎባጣ ሆኖ አላስኬድ የሚል ገደላገደል ቢያጋጥማችሁ በደምዳሜ እመር እያላችሁ አላፉት።»

ማስታወሻ

Tags:

ጳውሎስ ኞኞ የ ድርሰቶችጳውሎስ ኞኞ ጥቅስጳውሎስ ኞኞ ማስታወሻጳውሎስ ኞኞ1955ሥዕልስነ ጽሑፍኅዳር 11አርበኞችአዲስ ዘመን (ጋዜጣ)ኢትዮጵያድሬዳዋጣሊያን

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

ሊምፋቲክ ፍላሪያሲስቁርአንኮሶ በሽታየሒሳብ ምልክቶችየፈጠራዎች ታሪክጉንዳንየይሖዋ ምስክሮችአሜሪካማይልአሊ ቢራቅዱስ መርቆሬዎስገብረ ክርስቶስ ደስታ ግጥሞችሙቀትፋይዳ መታወቂያክራርፑንትሊያ ከበደከንባታጂጂጥርስአኻያተረት የየደም መፍሰስ አለማቆምየውሻ አስተኔያማርኛ ሰዋስው (1948)ዶቅማኣበራ ሞላየፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽንጠንበለልየአሜሪካ ዶላርደንደስየትንቢት ቀጠሮግብፅሲሳይ ንጉሱከኤች·አይ·ቪ ቫይረስ ጋር ተስማምቶ ለመኖርየአሜሪካ ፕሬዚዳንትኣሳማቤተ ማርያምንግድመስተዋድድዌብሳይትፌጦሥነ ውበትየአባይን ልጅ ውሀ ጠማው የላጭን ልጅ ቅማል በላውማርቲን ሉተርብርሃንየቅድስት ድንግል ማርያም ስሞችየኢትዮጵያ ሕገ መንግስትየማርቆስ ወንጌልጥምቀትመጽሐፈ ኩፋሌክብቅልጥ አለትሄክታርሃይል (ፊዚክስ)ቀረፋአቡነ ተክለ ሃይማኖትየኢትዮጵያ ካርታህግ ተርጓሚጃፓንአፈ፡ታሪክገዳዩ ባልሽ የሞተው ወንድምሽይሖዋጳውሎስግራዋዘረኝነትየንጥረ ነገሮች ሠንጠረዥየቅርጫት ኳስየዋና ከተማዎች ዝርዝርንግሥት ዘውዲቱኳታርፋሲለደስመንግሥተ አክሱምፋይናንስ🡆 More