ጦርነት ግዛቶች ወይም ኅብረተሠቦች በመሣሪያዎች ሲታገሉ ነው። በጦርነት ጊዜ ሥራዊቶቹ ብዙ ግፍና መግደል ሊያድርጉ ይቻላል። በጥንታዊ ግብጽ ጥንታዊ መንግሥት 3125-2763 ዓክልበ.
ግድም የሔሩ ወገን (የፈርዖኖች ወገን) ብዙ ጊዜ ጦርነት በአካባቢያቸው ሕዝቦች እንዳደረጉ ይታወቃል። በኋላ በመስጴጦምያ ታሪክ ኤላምና ኪሽ የተባሉት ጥንታዊ አገራት እርስ በርስ ጦርነት ጀመሩ (2384 ዓክልበ.)። በትንሽ ጊዜ ላይ ጦርነቶች በቻይና፣ በአፍሪቃና በአውሮፓ በየትም ተከሰቱ። ከዚያ ወዲህ ምንጊዜም በዓለም ላይ አንዳንድ ጦርነቶች በአንዳንድ አገራት ሊገኙ ይቻላል፤ በአንድም አገር ጦርነት በማይገኝበት ጊዜ ወይም ከተጨረሰ በኋላ ሰላም ይባላል።
የመንግሥታት ማህበርና ቀጥሎ የተባበሩት መንግሥታት የአለም አገራት ሰላም እንዲጠብቅ ሠርተዋል፣ ሆኖም በአንዳንድ ቦታ ጦርነት እስካሁን ድረስ ይከሠታል።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ጦርነት, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.