ጥርሶች በማንኛውም የጀርባ አጥንት ያላቸው እንስሳቶች አፍ ውስጥ ከድድ ጋር ተያይዘው የሚገኙ ነጫጭ፣ ጠንካራ፣ ስለታም እና ትናንሽ የአካል ክፍሎች ናቸው። እነዚህ አካላት በዋነኛነት ምግብን ለማድቀቅ ይጠቅማሉ። አንዳንድ ስጋ በል የሆኑ እንስሳት ይህን አካላቸውን እንደ አደን መሳሪያ ወይም እንደ ራስ መከላከያ መሳሪያነት ይጠቀሙበታል። ጥርሶች የተደረደሩበት ቦታ ድድ ይባላል። ጥርሶች ከአጥንት የተሠሩ ወይም አጥንቶች አይደሉም። ይልቁንም የተገነቡት የተለያየ እፍግታ እና ጥንካሬ ካላቸው ቁሶች ነው።
የሰው ና የተለያዩ እንስሳትን ጥርስ አጠቃላይ ቁጥር ለማስላት የራሱ የሆነ ቀመር አለው። እሱም ፤ የተሰጠ የፊት,ክራንቻ,ቀዳሚ መንጋጋ እና ድህረ መንጋጋ ጥንድ ቁጥሮችን በመደመር በ2 በማብዛት የእያንዳንዱን ጥንድ ጥርሶች ብዛት ካወቅን በሃላ ደምረን ማወቅ ይቻላል። # n+n.2+n+n.2+n+n.2+n+n.2
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ጥርስ, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.