የጎርጎርያን ካለንዳር ወይም በሌላ ስሙ የምዕራቡ ካሌንዳር በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው የቀናት አቆጣጠር ዘዴ ነው። ካሌንደሩን ያስተዋወቀው የሮማው ፓፓ ግሪጎሪ ፰ኛ ነበር። ካሌንደሩ በህዳር 24፣ 1582 ዓ.ም.
(እ.ኤ.አ) የጎርጎርያን ካሌንደር ተብሎ ተሰየመ፣ በአዋጅም ጸና። የአዲሱ ካሌንደር መነሻ ምክንያት የጁሊያን ካሌንደር በአንድ አመት ውስጥ 365.25 ቀንናቶች አሉ ብሎ ያስቀመጠው እምነቱ በ11 ደቂቃወች ከዕውነተኛው የአመት ርዝመት አንሶ መገኘቱ ነበር። ስለዚህም የጁሊያን ካሌንደር ከተሰራ ጀምሮ ፓፓው እስከ ቀየረው ድረስ የተጠራቀመው ስህተት 10ቀን ወጣው። ይህ የ10 ቀን ለውጥ የካቶሊክ ቤ/ክርስቲያናንን የፋሲካ በዓል ስላዛባ ካሌንደሩ መስተካከሉ የግድ ሆነ።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ጎርጎርያን ካሌንዳር, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.