ደረስጌ ማርያም ደባርቅ፣ ጎንደር ውስጥ ደረስጌ (ደብረ-ስጌ ከሚለው ስም የመጣ)፣እሚባል ቦታ የሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ነው። በዘመነ መሳፍንት ገነው የነበሩት ደጃች ውቤ እራሳቸውን ለማንገሥ ሲሉ የጀርመኑን ሠዓሊ እና ሳይንቲስት ዶክተር ሺምፐር በመቅጠር በ1840ዎቹ መጀመሪያ ያስገነቡት ቤተክርስቲያን ነው። በኋላ ላይ ከወደፊት ዓፄ ቴዎድሮስ ጋር በዚሁ አካባቢ ጦርነት ገጥመው ስለተሸነፉ ፣ ራስ ውቤ ለስርዓተ ንግሣቸው ባሠሩት ቤተ ክርስቲያን ዓፄ ቴዎድሮስ በአቡነ ሰላማ እጅ ተቀብተው ዘውድ ጭነው ነገሡበት። ይሄውም በ1847 መሆኑ ነው።
ደረስጌ ማርያም | |
ደረስጌ ማርያም | |
ከፍታ | 3035 ሜትር |
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ደረስጌ ማርያም, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.