ዩጋንዳ

ዩጋንዳ ሪፐብሊክ (ወይም ዑጋንዳ) በምስራቅ አፍሪካ የሚገኝ ሀገር ነው። በኬንያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ፣ ሩዋንዳ እና ታንዛኒያ ይዋሰናል። የዩጋንዳ ሰም የመጣው ከቡጋንዳ መንግሥት ነው።

Republic of Uganda
የዩጋንዳ ሬፑብሊክ

የዩጋንዳ ሰንደቅ ዓላማ የዩጋንዳ አርማ
ሰንደቅ ዓላማ አርማ
የዩጋንዳመገኛ
የዩጋንዳመገኛ
ዋና ከተማ ካምፓላ
ብሔራዊ ቋንቋዎች እንግሊዝኛስዋሂሊ
መንግሥት
ፕሬዚዳንት
 
ዮወሪ ሙሰቬኒ
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
 
236,040 (81ኛ)
ገንዘብ ሺሊንግ
ሰዓት ክልል UTC +3
የስልክ መግቢያ +256

ታሪክ

ከአረቦችና አውሮፓውያን በ1800ቹ ከመድረሳቸው በፊት ብዙ የሚታወቅ ነገር አልነበረም። በ15ተኛ መቶ ክፍለ-ዘመን ችዌዚ የተባለውን መንግስት በአፈ ታሪክ ይገኛል። አረቦችና አውሮፓውያን በ19ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን ሲደርሱ ብዙ መንግሥቶች በቦታው ነበሩ። እነዚህም በንዮሮ ፣ ቡሶጋ ፣ ቡጋንዳ ፣ ቶሮ እና አንኮልን ያጠቃልላሉ። ከ1894 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በታላቁ ብሪታን ስትመራ ነበር። የተለያዩ ቦታዎች ከተዋሃዱ በኋላ ዩጋንዳ በ1914 እ.ኤ.አ. ቅርጿን ያዘች።

1966 እ.ኤ.አ. ጠቅላይ ሚኒስትር ሚልተን ኦቦቴ ሕገ-መንግሥቱን አፍርሰው እራሳቸውን ፕሬዝዳንት አደረጉ። በ1971 እ.ኤ.አ. ኢዲ አሚን ሀገሩን መምራት ጀመሩ። የኢዲ አሚን አመራር 300,000 የሚገመቱ ዩጋንዳውያንን አስጨርሷል። በ1979 እ.ኤ.አ. የታንዛንያ ኃይሎች ኢዲ አሚንን ከሥልጣን ያስወግዳሉ። ሚልተን ኦቦቴ ወደ ሥልጣን ይመለሳሉ ግን በ1985 እ.ኤ.አ. እንደገና ይወርዳሉ። ያሁኑ ፕሬዝዳንት ዮወሪ ሙሴቪኒ ከ1986 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በሥልጣን ላይ ናቸው።

ፖለቲካ

ዩጋንዳ 
ዮወሪ ሙሴቪኒ

ፕሬዝዳነንቱ አንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ይመርጣሉ። ያሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አፖሎ ሲባምቢ ናቸው።

መልከዓ-ምድር

ዩጋንዳ በመሬት የተቆለፈች ብትሆንም ታላላቅ የውሃ አካላት አሉ። ከነዚህ ውስጥም ቪክቶሪያ ሐይቅ፣ አልበርት ሐይቅ፣ ክዮጋ ሐይቅ እና ኤድዋርድ ሐይቅ ይዘረዘራሉ። ታላላቅ ከተማዎች በቪክቶሪያ ሐይቅ አቅራቢያ ይገኛሉ። እነዚህም ካምፓላንና እንትቤን ያጠቃልላል።

ዩጋንዳ በ70 ወረዳዎች የተከፋፈለች ስትሆን እነዚህም በአራት አመራር ክልሎች ውስጥ ናቸው። አራቱ አመራር ክልሎች ሰሜናዊ ፣ ምሥራቃዊ ፣ ማዕከላዊ እና ምዕራባዊ ይባላሉ። ወረዳዎቹ በዋና ከተማዎቻቸው ነው የሚሰየሙት።

ኤኮኖሚ

በዩጋንዳ ውስጥ የመዳብ እና ነጭ ብረት ክምችቶት አሉ። ግብርና ዋናው የኤኮኖሚ ሴክተር ነው። ከ80 በመቶ በላዩ የስራ ኃይል በግብርና ነው የተሰማራው። ቡና ዋናው የኤክስፖርት ትርፍ ምንጭ ነው። ከ1986 እ.ኤ.አ. ጀምሮ መንግሥቱ ከሌሎች ሀገሮችና ዓለምአቀፍ ድርጅቶች ጋር በመሆን በኢዲ አሚን ጊዜ የወደቀውን ኤኮኖሚ ለማንሳት ተጣጥሯል።

የሕዝብ እስታቲስቲክስ

ዩጋንዳ ለብዙ ብሔረሰቦች ቤት ነው። ከነዚህ ውስጥ ግን አንድ ትልቁን ሕዝብ ብዛት የሚወክል የለም። 40 አካባቢ የሚሆኑ ቋንቋዎች ባሁኑ ጊዜ ይነገራሉ። ከነጻነት በኋላ እንግሊዝኛ ብሔራዊ ቋንቋ ተደርጓል። ብዙ ተናጋሪዎች ያሉት ቋንቋ ሉጋንዳ ሲሆን የአቴሶ ቋንቋ በሁለተኛነት ይከተላል። ኪስዋሂሊ ዋናው የንግድ ቋንቋ ነው።

ግንኙነት

ስልክ፦

  • መስመሮች - 54,074 (1998 እ.ኤ.አ.)
  • የእጅ ስልኮች - 9,000 (1998 እ.ኤ.አ.)

ራዲዮ

  • ማሰራጫ ስቴሽኖች - AM 19, FM 4
  • ራዲዮኖች - 2.6 ሚሊዮን (1997 እ.ኤ.አ.)

ቴሌቪዥን

  • ማሰራጫ ስቴሽኖች - 8
  • ቴሌቪዥኖች - 315,000 (1997 እ.ኤ.አ.)

ኢንተርኔት

  • የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢዎች - 3 (1999 እ.ኤ.አ.)
  • የኢንተርኔት ሀገር ኮድ - .ug

ትምህርት

የዩጋንዳ የትምህርት ስርዐት የሰባት ዓመት መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት፣ ስድስት ዓመት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እና ከ3 እስከ 5 ዓመት ከሁለተኛ ደረጃ በኃላ ትምህርት ያጠቃልላል። የትምህርት ስርዐቱ ከ1960ዎቹ እ.ኤ.አ. ጀምሮ በሥራ ላይ ውሏል።

ትራንስፖርት

  • አጠቃላይ የባቡር መንገድ - 1,241 ኪ.ሜ.
  • አጠቃላይ መንገድ ርዝመት - 27,000 ኪ.ሜ.
  • ሄሊኮፕተር ማረፊያ - 2

አውሮፕላን ማረፊያ

  • ዋና - እንትቤ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ
  • ጠጠር የለበሱ - 4
  • ጠጠር ያለበሱ - 22


Tags:

ዩጋንዳ ታሪክዩጋንዳ ፖለቲካዩጋንዳ መልከዓ-ምድርዩጋንዳ ኤኮኖሚዩጋንዳ የሕዝብ እስታቲስቲክስዩጋንዳ ግንኙነትዩጋንዳ ትምህርትዩጋንዳ ትራንስፖርትዩጋንዳምስራቅ አፍሪካሩዋንዳታንዛኒያኬንያኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክደቡብ ሱዳን

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

የኢትዮጵያ አየር መንገድሀመርየወንዶች ጉዳይቫስኮ ደጋማትዝታኸፊንግተን ፖስትሸዋየፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን22 Marchፍልስፍናቁልቋልፋሲል ግቢእንዶድኦሮማይአፈ፡ታሪክየጋብቻ ሥነ-ስርዓትየኢትዮጵያ የ5 ሺ ዓመት ታሪክ ከኖኅ እስከ ኢህአዴግባቢሎንየቃል ክፍሎችየተባበሩት የሀገር ንጉሳዊ አገዛዝእንጦጦዚምባብዌሥልጣናዊነትእሪያኩሽ (የካም ልጅ)ደቡብ ኮርያአማርኛጭፈራመስተዋድድአድዋደርግየኖህ ልጆችወላይታአንዶራ ላ ቬላአቡነ ተክለ ሃይማኖትአብርሐምፋሲለደስገብረ መስቀል ላሊበላመጽሐፈ ሲራክዓፄ ቴዎድሮስማናልሞሽ ዲቦጋምቤላ (ከተማ)የአድዋ ጦርነትልብአቡነ ሰላማፊኒክስ፥ አሪዞናጎንደር ከተማዲ ኤን ኤስዕልጀጎል ግንብፈሊጣዊ አነጋገር የየኦሎምፒክ ጨዋታዎችዓለም-አቀፍ መደበኛ የመጽሐፍ ቁጥርወፍነነዌኦክሲጅንደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልልአንዶራሲቪል ኢንጂነሪንግስፖርትቤተ መርቆሬዎስወንዝኦሮምኛየንቅያ ጸሎተ ሃይማኖትየማርቆስ ወንጌልወለተ ጴጥሮስወደፊት ገስግሺ ውድ እናት ኢትዮጵያራስኮረሪማየድመት አስተኔ🡆 More