ዩክሊድ

ዩክሊድ ወይንም የእስክንድርያው ዩክሊድ ( 325 ዓ.ዓ.–265 ዓ.ዓ.) የጥንቱ ዘመን ገናና የሒሳብ ተማሪ ነበር። ዩክሊድ እስክንድርያ፣ ግብፅ አገር በእስክንድርያ ቤተ መጻሕፍት ተቀጥሮ ይሰራ ነበር። ከዘመኑ ርዝመትና ከመዝገብ መጥፋት አንጻር፣ የዩክሊድ ህይወት ታሪክ እምብዛም አይታወቅም።

ዩክሊድ
የዩክሊድ ሃውልት፣ በኦክስፎርድእንግሊዝ

ኢለመንትስ (ታዋቂው የዩክሊድ መጽሐፍ)

ዩክሊድ፣ የነበረበትን ዘመን የጂዎሜትሪ ዕውቀት በማሰባሰብ ኤሌመንትስ የተሰኘውን መጽሐፍ ለመድረስ ቻለ። ይህ መጽሐፍ ከጥንት ጀምሮ እስከ አሁን ዘመን ድረስ ለጅዎሜትሪ ትምህርት መሰረት ሆኖ ያገለግላል።

የዩክሊድ መጽሐፍ ከአንስተኛ ቁጥር ያላቸው የጂዎሜትሪ እሙኖች በመነሳት አምክንዮን በመጠቀም ወደ ብዙ እርግጦች በመሻገር የጂዎሜትሪና የቁጥር ጠባያትን ከጥርጥር ውጭ በሆነ መልኩ ይገልጻል።

የኤለመንትስ መጽሐፉ፣ በተጨማሪ፣ ስለእይታ (ፔሬስፔክቲቭ)፣ የሾጣጣ ክፍሎች፣ ሉላዊ ጂዎሜትሪ እና ኳድራቲክ ገጽታዎች ያትታል። ከጂዎሜትሪ ጎን ለጎን የቁጥር ኅልዮትም በሚገባ መልኩ በዚሁ መጽሐፍ ተመርምሯል። ታላቁ የጋራ አካፋይ የተሰኘውን የሥነ ቁጥር መሳሪያ በዚሁ መጽሐፍ በዩክሊድ ተደርሶ ይገኛል።

ዩክሊድ ያስቀመጠው የጂዎሜትሪ ስርዓት ለብዙ ዘመናት ጅዎሜትሪ በመባል ሲታወቅ፣ እስከ 19ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ እንደ ብቸኛ ጂዎሜትሪ ይወሰድ ነበር። ሆኖም ግን በዚሁ ዘመን በተነሱ ሌሎች አይነቶች ጂዎሜትሪዎች፣ የርሱ ስርዓት ዩክሊዳዊ ጅዎሜትሪ በመባል ይታወቃል። ይሄውም ከኢ-ዩክሊዳዊ ጅዎሜትሪ ልዩ መሆኑን ለማሳየት ነው።

ከኤሌመንትስ በተጨማሪይ የዩክሊድ ሌሎች 5ስራዎች እስከ አሁን ዘመን ድረስ ዘልቀው ይገኛሉ። እኒህ 5 ስራዎች በይዘታቸው ከኤልመንትስ ጋር ተመሳሳይ ናቸው።

ዩክሊድ 
እጅግ ጥንታዊ የሆነ የዩክሊድ ኤሌመንትስ መጽሐፍ ቅሪት (100 ዓ.ም.) ። ምስሉ ከኤሌመንትስ መጽሐፍ 2፣ እርግጥ 5 ይመነጫል


ማጣቀሻ

Tags:

ሒሳብእስክንድርያግብፅ

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

ኒሳ (አፈ ታሪክ)ገናግስበትጸሐፌ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴ ወልደ አረጋዊየጋብቻ ሥነ-ስርዓትጣይቱ ብጡልሀይቅተውሳከ ግሥካይሮብርብራየሥነ፡ልቡና ትምህርትእያሱ ፭ኛቅኔማህበራዊ ሚዲያቼኪንግ አካውንትሀዲያቡናተስፋዬ ሳህሉሲዳምኛአዕምሮበገናዳግማዊ ምኒልክየሐበሻ ተረት 1899ሽመናሰምና ፈትልቺኑዋ አቼቤቁስ አካልሰንኮፉ አልወጣምአድዋወገርትጂዎሜትሪስንዝር ሲሰጡት ጋትየሂንዱ ሃይማኖትፈሊጣዊ አነጋገርባቡርሶዶቀዳማዊ ቴዎድሮስሐና ወኢያቄምአምበሾክቻይንኛአፋር (ክልል)ገብረ ክርስቶስ ደስታ ግጥሞችሻይ ቅጠልኦክሲጅንጳውሎስኢትዮ ቴሌኮምመስተፃምርስእላዊ መዝገበ ቃላትፈቃድመስቀልፊሊፒንስመንፈስ ቅዱስዓረፍተ-ነገርቤተ ሚካኤልተከዜማርያምጉሬዛብር (ብረታብረት)የወታደሮች መዝሙርጣና ሐይቅጊዜዋአፋር (ብሔር)የመስቀል ጦርነቶችየነቶሎ ቶሎ ቤት ግድግዳው ሰንበሌጥሥነ ንዋይ23 Aprilፈረንሣይሳላ (እንስሳ)የሒሳብ ምልክቶችትምህርትእስራኤልባቲ ቅኝትላሊበላጃፓንኛ🡆 More