የኢትዮጵያ ነገሥታት

የኢትዮጵያ ነገሥታት ለብዙ ዘመናት ኢትዮጵያን ሲያስተዳድሩ ቆይተዋል።

ታሪክ

በመጀመሪያ ከሰብታህ ጀምሮ እስከ ጲኦሪ አንደኛ ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ፳፭፻፵፭ እስከ ፲፱፻፹፭ ዓመት ከነገደ ካም በኢትዮጵያ የነገሡ ነገሥታት ፳፪ ናቸው፤ ዘመኑም ፭፻፷ ይሆናል።

ከክርስቶስ ልደት በፊት ነገደ ዮቅጣን መንገሥ ከጀመሩበት ፲፱፻፹፭ ዓመት ጀምሮ ቀዳማዊ ምኒልክ እስከ ነገሡበት እስከ ፱፻፹፪ ዓመት አግዓዝያን ከተባሉ ከነገደ ዮቅጣን በኢትዮጵያ የነገሡ ነገሥታት ፶፪ ናቸው። ዘመኑም ፩ ሺህ ፫ ዓመት ይሆናል።

ከክርስቶስ ልደት በፊት ቀዳማዊ ምኒልክ ከነገሡበት ከ፱፻፹፪ ዓመት ጀምሮ ክርስቶስ እስከ ተወለደበት እስከ ፩ ዓመተ ምሕረት እስከ ባዚን በኢትዮጵያ የነገሡ ነገሥታት ፷፯ ናቸው። ዘመኑም ፱፻፹፪ ይሆናል። ነገር ግን ባዚን ከክርስቶስም ልደት በኋላ ፱ ዓመት ነግስዋልና ይህ ሲጨመር ፱፻፺፩ ይሆናል።

ከባዚን ጀምሮ የቀዳማዊ ምኒልክ መንግሥት ወደ ነገደ ዛጔ እስከ ፈለሰበት እስከ ድልነዓድ ድረስ ከ፩ እስከ ፱፻፲፪ ዓመተ ምሕረት በኢትዮጵያ የነገሡ ነገሥታት ፺፬ ናቸው። ነገር ግን ባዚን ሁለት ጊዜ ያልተቆጠረ እንደ ሆነ ፺፫ ይሆናል። ዘመኑም ፱፻፲፪ (፱፻፳) ዓመት ይሆናል። ክርስትና በኢትዮጵያ የገባው በነዚሁ ዓመታት ውስጥ ከ፪፻፺፰ እስከ ፫፻፳፬ ዓ.ም. በአብርሃና አጽብሓ ዘመን ነው።

ከድልነዓድ በኋላ ከመራ ተክለ ሃይማኖት (ስመ መንግሥታቸው ዛጔ) ጀምሮ እስከ ይትባረክ በኢትዮጵያ ነገሡ የዛጔ ወገኖች ፲፩ ነገሥታት ናቸው። ዘመኑም ፫፻፴፫ ዓመት ይሆናል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በኃይል ወደ ዛጔ ዘር ካለፈ በኋላ በ፫፻፴፫ ዓመት እንደ ገና ወደ ቀዳማዊው ምኒልክ ዘር ወደ ይኩኖ አምላክ ከተመለሰበት ከ፲፪፻፵፭ (፲፪፻፶፫) ዓ.ም. ጀምሮ የጎንደር መንግሥት እስከሚባለው ሠርፀ ድንግል እስከ ነገሡበት እስከ ፲፭፻፶፫ ዓ.ም. በኢትዮጵያ የነገሡ ነገሥታት ፳፮ ናቸው፤ ዘመኑም ፫፻፩ ዓመት ይሆናል።

ሠርፀ ድንግል ከነገሠበት ከ፲፭፻፶፫ እስከ ፲፯፻፸፯ ዓ.ም.

የጎንደር መንግሥት መጨረሻ እስከ ተክለ ጊዮርጊስ፤ በጎንደር ቤተ መንግሥት ሆነው ኢትዮጵያን የገዙ ነገሥታት ፲፰ ናቸው። ዘመኑም ፪፻፹፬ ዓመት ይሆናል። 

የጎንደር መንግሥት የሚባለው ከተጨረሰበት ከ፲፯፻፸፯ ዓ.ም. ጀምሮ ዓፄ ቴዎድሮስ እስከ ነገሡበት እስከ ፲፰፻፵፭ የገዙ መሳፍንት ፲፱ ናቸው። በነዚህም መሳፍንት ዘመን ሙሉ ሥልጣን ሳያገኙ ለስሙ ብቻ ዘውድ እየጫኑ በጎንደር ቤተ መንግሥት ይቀመጡ የነበሩ ትውልዳቸው ከቀዳማዊ ምኒልክ ወገን የሆኑ ነገሥታት ፲፬ ናቸው።

ዘመነ መሳፍንት ካለፈ በኋላ ከ፲፰፻፵፭ እስከ ፲፰፻፹፩ በኃይልና በጉልበት የነገሡ የኢትዮጵያ ነገሥታት ፫ ናቸው። ዘመኑም ፴፮ ዓመት ይሆናል።

የሸዋ መንግሥት ባላባቶች ፲፭ ናቸው። የግዛታቸውም ዘመን ፪፻፸ ዓመት ይሆናል።

ዝርዝር

አለቃ ታዬ በ1906 ዓ.ም ከጻፉት የኢትዮጵያ የሕዝብ ታሪክ፣ ኅሩይ ወልደሥላሴ በ1913 ዓ.ም. ከጻፉት ዋዜማ፣ እና በ1919 ዓ.ም. ራስ ተፈሪ (በኋላ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ለቻርልስ ረይ ካቀረቡት ዝርዝር የተወሰደው ልማዳዊ ነገሥታት ዝርዝር እዚህ ታች ይከተላል።

ነገደ ኦሪ

(እነኚህ ነገሥታት ከማየ አይህ አስቀድሞ በኢትዮጵያ የነገሡ ሲባል ከአፈ ታሪክ ይገኛል።)

  1. ኦሪ 60 ዓመት
  2. 1 ጋርያክ 66
  3. ጋንካም 83
  4. ንግሥት ቦርሳ 67
  5. 2 ጋርያክ 60
  6. 1 ጃን 80
  7. 2 ጃን 60
  8. ሰነፍሩ 20
  9. ዘእናብዛሚን 58
  10. ሳህላን 60
  11. ኤላርያን 80
  12. ኒምሩድ 60
  13. ንግሥት ኤይሉካ 45
  14. ሳሉግ 30
  15. ኃሪድ 72
  16. ሆገብ 100
  17. ማካውስ 70
  18. አሳ 30
  19. አፋር 50
  20. ሚላኖስ 62
  21. ሶሊማን ታጊ 73 አመት - የጥፋት ውኃ የደረሰበት ዘመን ይባላል።

ነገደ ካም ወይም ነገደ ኩሳ (የኩሽ ነገሥታት)

  1. ካም - ከባቢሎን ግንብ ውድቀት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ገባ፣ ለ78 ዓመታት ነገሠ። ከዚያ ሶርያን በወረረበት ጊዜ ተገደለ።
  2. ኩሳ - 50 ዓመት ነገሠ።
  3. ሀባሢ - 40 ዓመት
  4. ሰብታ - 30 ዓመት
  5. ኤሌክትሮን - 30
  6. ነቢር - 30
  7. 1 አሜን - 21
  8. ንግሥት ነሕሴት ናይስ (ካሲዮኔ) - 30 ዓመት ነገሰች፤ የሲኒ ከነዓን ልጆች ወደ ኩሽ ገቡ።
  9. ሆርካም - 29 ዓመት፣ የአርዋዲ ከነዓን ልጅ አይነር ወደ ኩሽ ገባ።
  10. 1 ሳባ - 30 ዓመት፣ ዋቶ ሳምሪ ከነዓን (ፋይጦን) ወደ ኩሽ ገባ።
  11. ሶፋሪድ - 30
  12. እስከንዲ - 25
  13. ሆህይ - 35
  14. አህያጥ - 20
  15. አድጋስ - 30
  16. ላከንዱን - 25
  17. ማንቱራይ - 35
  18. ራክሁ - 30
  19. 1 ሰቢ - 30
  20. አዘጋን - 30
  21. ሱሹል አቶዛኒስ - 20
  22. 2 አሜን - 15
  23. ራመንፓህቲ - 20
  24. ዋኑና - 3 ቀን
  25. 1 ጲኦሪ - 15 አመት። የሕንድ ንጉሥ ራማ ኩሽን ወረረ፤ በኋላ የሣባ ነገሥታት በኩሽ ይገዛሉ።

ነገደ ዮቅጣን ወይም አግአዝያን (የሣባ ነገሥታት)

  1. አክሁናስ 2 ሳባ -55 ዓመት ነገሠ
  2. ነክህቲ ካልንስ - 40
  3. ንግሥት ካሲዮጲ - 19
  4. 2 ሰቢ - 15 አመት። የሐማቲ ከነዓን ልጆች ወደ ኢትዮጵያ ገቡ።
  5. 1 ኢትዮጲስ - 56
  6. ላከንዱን ኖወር አሪ - 30 አመት። የኢትዮጲስ ልጅ።
  7. ቱት ኤምሄብ - 20
  8. ሔርሐቶር - 20
  9. 2 ኢትዮጲስ - 30
  10. 1 ሰኑካ - 17
  11. 1 ቦኑ - 8
  12. ንግሥት ሙማዜስ - 4
  13. ንግሥት አሩአስ - 7 ወር - የሙማዜስ ልጅ
  14. አሚን አስሮ - 30 አመት
  15. 2 ኦሪ - 30
  16. 2 ጲኦሪ - 15
  17. 1 አሜን ኤምሐት - 40
  18. ፃውዕ - 15
  19. አክቲሳኒስ - 10 ዓመት። በዲዮዶሮስ ዘንድ ግብጽን ያዘ።
  20. ማንዲስ - 17 ዓመት። በዲዮዶሮስ ዘንድ በግብጽም ገዛ
  21. ጵሮቶውስ - 33 ዓመት። በትሮያ ጦርነት ዘመን በግብጽም እንደ ገዘ በግሪክ ጸሓፍት ተባለ።
  22. አሞይ - 21
  23. ኮንሲ (ሕንዳዊ) - 5
  24. 2 ቦኑ - 2
  25. 3 ሰቢ - 15 አመት። የቦኑ ልጅ
  26. ጀጎንስ - 20
  27. 2 ሰኑካ - 10
  28. 1 አንጋቦ - 50 አመት። አርዌን የገደለው።
  29. ሚአሙር - 2 ቀን
  30. ንግሥት ከሊና - 11 አመት
  31. ዘግዱር - 40 ዓመት - የግዕዝ ፊደል (ተናባቢዎች) እንደ ፈጠረ ይባላል።
  32. 1 ሔርሐቶር ኤርትራስ - 30
  33. 2 ሔርሐቶር - 1
  34. ኔክቴ - 20
  35. ቲቶን ሶትዮ - 10
  36. ሔርመንቱ - 5 ወር
  37. 2 አሜን ኤምሐት - 5 ዓመት
  38. 1 ኮንሳብ - 5
  39. 2 ኮንሳብ - 5
  40. 3 ሰኑካ - 5
  41. 2 አንጋቦ ሕዝባይ - 40
  42. አሜን አስታት - 30
  43. ሔርሆር - 16 አመት። የቴብስ ካህን፤ ደግሞ በግብጽ ገዛ
  44. 1 ፒያንኪያ - 9 አመት። የቴብስ ካህን
  45. 1 ፕኖትሲም - 17 አመት።
  46. 2 ፕኖትሲም - 41 አመት። የቴብስ ካህን፤ ደግሞ በደቡብ ግብጽ ገዛ
  47. ማሳሔርታ - 16 አመት። የቴብስ ካህን
  48. ራመንከፐር - 14 አመት። የቴብስ ካህን፤ ደግሞ በደቡብ ግብጽ ገዛ
  49. 3 ፒኖትሲም - 7 ዓመት። የቴብስ ካህን፤ ደግሞ በደቡብ ግብጽ ገዛ
  50. 4 ሰቢ - 10 አመት
  51. ተዋስያ ዴውስ - 13
  52. ንግሥት ማክዳ - 31 ዓመት። የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን የጎበኘች።

ከ ቀዳማዊ ምኒልክ እስከ ባዜን

  1. ቀዳማዊ ምኒልክ - 25 ዓመት - የሰሎሞን ልጅ
  2. ሃንድዮን 1 ሲራህ - 26 ዓመት
  3. አመንሆቴፕ ቶማ - 31
  4. አክሱማይ ራሚሱ ዘግዱር - 20
  5. አውስዮ 2 ሲራህ - 38
  6. 1 ሻባካ - 21
  7. 2 ፒያንኪ አብራልዩስ - 32 ዓመት - ደግሞ በግብጽ ገዛ
  8. አክሱማይ - 23
  9. ካሽታ - 13 ዓመት፣ ደግሞ በግብጽ ገዛ
  10. 2 ሻባካ - 12 ዓመት - ደግሞ በግብጽ ገዛ
  11. ንግሥት ኒካንታ ቅንዳኬ - 10
  12. ታርሐቅ - 49 ዓመት - ደግሞ በግብጽ ገዛ
  13. እርዳመን አውስያ - 6 ዓመት
  14. ጋሲዮ - 6 ሰዓት
  15. ታኑታሙን - 4 ዓመት - ደግኖ በግብጽ ገዛ
  16. ቶማድዮን 3 ፒያንኪ - 12 ዓመት

ከዓጼ ዘርዐ ያዕቆብ (1426 ዓ.ም.) ወዲህ

በ፲፬፻፳፮ ዓ.ም. ከነገሡት ከዓጼ ዘርዐ ያዕቆብ ወዲህ ያሉት የኢትዮጵያ ነገሥታት ስማቸውና የግዛታቸው ዘመን ከዚህ በታች ይገኛሉ።

ስም ስመ መንግሥት (የግብር ስም) አባት ግዛት ዓመታት ዓመተ ምሕረት
ዓጼ

ዘርዐ ያዕቆብ

ቁስጠንጢኖስ ቀዳማዊ ዳዊት ፴፬ ፲፬፻፳፮ - ፲፬፻፷
ዓጼ በእደ ማርያም ዓጼ ዘርዐ ያዕቆብ ፲፬፻፷ - ፲፬፻፸
ዓጼ እስክንድር ዓጼ በአደ ማርያም ፲፮ ከ፭ ወር ፲፬፻፸ - ፲፬፻፹፮
ዓጼ ዐምደ ጽዮን ዓጼ እስክንድር ፲፬፻፹፯
ዓጼ ናዖድ አንበሳ ዘፀር ዓጼ በአደ ማርያም ፲፫ ፲፬፻፹፯ - ፲፭፻
ዓጼ ልብነ ድንግል ወናግ ሰገድ ዓጼ ናዖድ ፵፪ ፲፭፻ - ፲፭፻፴፫
ዓጼ ገላውዴዎስ አጽናፍ ሰገድ ዓጼ ልበነ ድንግል ፲፱ ፲፭፻፴፫ - ፲፭፻፶፩
ዓጼ ሚናስ አድማስ ሰገድ ዓጼ ልብነ ድንግል ፲፭፻፶፩ - ፲፭፻፶፭
ዓጼ ሠርፀ ድንግል መለክ ሰገድ ዓጼ ሚናስ ፴፬ ፲፭፻፶፭ - ፲፭፻፹፰
ዓጼ ያዕቆብ ዓጼ ሚናስ ፲፭፻፹፰ - ፲፭፻፺፭
ዓጼ ዘድንግል አቤቶ ልሳነ ክርስቶስ (እሳቸውም የዓጼ ሚናስ ልጅ) ፲፭፻፺፭ - ፲፭፻፺፯
ዓጼ ሱስንዮስ ሥልጣን ሰገድ አቤቶሁን ፋሲል (እሳቸውም የዓጼ ልብነ ድንግል የልጅ ልጅ) ፳፯ ፲፭፻፺፯ - ፲፮፻፳፬
ዓጼ ፋሲል ዓለም ሰገድ ዓጼ ሱስንዮስ ፴፮ ፲፮፻፳፬ - ፲፮፻፷
ቀዳማዊ ዓፄ ዮሐንስ አእላፍ ሰገድ ዓጼ ፋሲል ፲፭ ፲፮፻፷ - ፲፮፻፸፬
ቀዳማዊ ዓፄ ኢያሱ አድያም ሰገድ ቀዳማዊ ዓጼ ዮሐንስ ፳፬ ፲፮፻፸፬ - ፲፮፻፺፰
ዓጼ ተክለ ሃይማኖት ሉል ሰገድ ቀዳማዊ ዓጼ ኢያሱ ፲፮፻፺፰ - ፲፯፻
ዓጼ ቴዎፍሎስ አጽራር ሰገድ ቀዳማዊ ዓጼ ዮሐንስ ፫ ከ፫ ወር ፲፯፻ - ፲፯፻፫
ዓጼ ዮስጦስ ደዳዝማች ድል በኢየሱስ ፲፯፻፫ - ፲፯፻፰
ዳግማዊ ዓጼ ዳዊት አደባር ሰገድ ቀዳማዊ ዓጼ ኢያሱ ፲፯፻፰ - ፲፯፻፲፫
ዓጼ በካፋ መሲሕ ሰገድ ቀዳማዊ ዓጼ ኢያሱ ፲፯፻፲፫ - ፲፯፻፳፫
ዳግማዊ ዓጼ ኢያሱ ብርሃን ሰገድ ዓጼ በካፋ ፳፭ ፲፯፻፳፫ - ፲፯፻፵፯
ዓጼ ኢዮአስ ዳግማዊ ዓጼ ኢያሱ ፲፭ ፲፯፻፵፯ - ፲፯፻፷፫
ዳግማዊ ዓጼ ዮሐንስ ዘዋሕድ እዴሁ ቀዳማዊ ዓጼ ኢያሱ ፭ ወር ፲፯፻፷፫
ዳግማዊ ዓጼ ተክለ ሃይማኖት አድማስ ሰገድ ዳግማዊ ዓጼ ዮሐንስ ፲፯፻፷፫ - ፲፯፻፸
ቀዳማዊ ሰሎሞን ዮሐንስ ዳግማዊ ዓጼ ዳዊት ፲፯፻፸ - ፲፯፻፸፪
ቀዳማዊ ዓጼ ተክለ ጊዮርጊስ ፈጻሜ መንግሥት ዳግማዊ ዓጼ ዮሐንስ ፲፯፻፸፪ - ፲፯፻፸፯
ዘመነ መሳፍንት
ራስ ዓሊ (ትልቁ) አባ ሴሩ ጓንጉል ፲፯፻፸፯ - ፲፯፻፹፩
ራስ ዓሊጋዝ አባ ሴሩ ጓንጉል ፲፯፻፹፩ - ፲፯፻፹፮
ራስ ዐሥራትና ራስ ወልደ ገብርኤል ፲፯፻፹፮ - ፲፯፻፺፪
ራስ ጉግሣ መርሶ በሬንቶ ፳፮ ፲፯፻፺፪ - ፲፰፻፲፰
ራስ ይማም ራስ ጉግሣ ፲፰፻፲፰ - ፲፰፻፳
ራስ ማርዬ ራስ ጉግሣ ፲፰፻፳ - ፲፰፻፳፫
ራስ ዶሪ ራስ ጉግሣ ፫ ወር ፲፰፻፳፫
ራስ ዓሊ (ትንሹ) ደጃች አሉላ ፳፪ ፲፰፻፳፫ - ፲፰፻፵፭
ነገሥታት
ዓፄ ቴዎድሮስ አባ ታጠቅ ቋረኛ ኅይሉ ወልደ ጊዮርጊስ ፲፭ ፲፰፻፵፭ - ፲፰፻፷
ዳግማዊ ዓጼ ተክለ ጊዮርጊስ ዋግሹም ጎበዜ ገብረ መድኅን ፲፰፻፷ - ፲፰፻፷፫
ዓፄ ዮሐንስ አባ በዝብዝ ሹም ተምቤን ምርጫ ፲፰ ፲፰፻፷፬ - ፲፰፻፹፩
ዳግማዊ ዓጼ ምኒልክ አባ ዳኘው ንጉሥ ኃይለ መለኮት (እሳቸውም የንጉሥ ሣህለ ሥላሴ ልጅ) ፳፬ ፲፰፻፹፩ - ፲፱፻፮
ልጅ ኢያሱ አባ ጤና ንጉሥ ሚካኤል ፲፱፻፮ - ፲፱፻፱
ንግሥት ዘውዲቱ ዳግማዊ ዓጼ ምኒልክ ፲፫ ፲፱፻፱ - ፲፱፻፳፪
ቀዳማዊ፡ኃይለ፡ሥላሴ አባ ጠቅል ልዑል ራስ መኮንን (እሳቸውም የንጉሥ ሣህለ ሥላሴ የልጅ ልጅ)

ምንጭ

  • ዮሐንስ ወልደ ማርያም፣ የዓለም ታሪክ - ከጂዎግራፊ ጋር የተያያዘ፤ ፲፱፻፴፮ ዓ.ም.

Tags:

የኢትዮጵያ ነገሥታት ታሪክየኢትዮጵያ ነገሥታት ዝርዝርየኢትዮጵያ ነገሥታት ምንጭየኢትዮጵያ ነገሥታትኢትዮጵያ

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

ፈተና፤ የዕንባ ጉዞዎች እና ሌሎች ግጥሞችወርቅአትክልትወንዝፌጦተዋህዶቀነኒሳ በቀለየፀሐይ ሥርዓተ ፈለክአለማየሁ ፋንታዓፄ ነዓኩቶ ለአብንብሮማንያወሎቆለጥየስልክ መግቢያየላሊበላ ከፍልፍል ድንጋይ የተሠሩ አብያተ ክርስቲያናትገብረ ክርስቶስ ደስታጋሞሰባአዊ መብቶችምጣኔ ሀብትቼልሲየዓለም ሀገራት ባንዲራዎችቱርክየዮሐንስ ራዕይሕግአበራ ለማዶሮተራጋሚ ራሱን ደርጋሚኤችአይቪዳማ ከሴየታኅሣሥ ግርግርቋንቋዩኔስኮጋምቤላ ሕዝቦች ክልልሐመልማል አባተአቡነ ሰላማየዮሐንስ ወንጌልመስጊድሰማይ አንጎደጎደሙላቱ አስታጥቄዮሐንስ ፬ኛሸለምጥማጥመንግስቱ ኃይለ ማርያምአጭር የአማራ ማታገያ ሀሳብየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንአፍሮ እስያዊ ቋንቋዎችቅርንፉድባሕር-ዳርሶማሊያማሪኦአንኮር ዋትየ2010 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫአልባኒያራያአሰፋ አባተኤፕሪልማዳጋስካርበዓሉ ግርማእስራኤልካውናስአፋር (ክልል)መብረቅመጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤልምዕራብ አፍሪካኃይሌ ገብረ ሥላሴየኢትዮጵያ ሶማሊያ ጦርነትመጋቢትአልጀብራሳዳም ሁሴንሽኮኮከርከሮዲሜትሪ ሜንደሊቭቀልዶች ከጋብሮቮ ምድርየወታደሮች መዝሙር🡆 More