የትነበርሽ ንጉሴ በኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ እና የአካል ጉዳተኛ መብትቶች ተሟጋች ናት ፡ እ.ኤ.አ በ 2017 የአካል ጉዳተኞችን መብቶችን እና ማካተቶችን በማስተዋወቅ እንዲሁም በማኅበረሰቡ ውስጥ ያሉየአእምሮ ውቅርን መለወጥ የሚያበረታታ ሥራዋ ራይት ላይቭሊሁድ ኣዋርድን ተሸልማለች።
የትነበርሽ ንጉሴ የአይን ብርሃኗን ያጣችው በ 5 ዓመቷ ነበር ። ይህ አጋጣሚ በተወለድችበት በአማራ ክልል በስፋት ይተገበር ከነበረው ያለ አድሜ ጋብቻ አንድታመልጥ እድሉን እንደፈጠረላት ትናገራለች። ፡፡የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቷን በሻሸመኔ ካቶሊክ የዓይነ ስውራን ት/ቤት ተከታትላ ወደ ዳግማዊ ምኒልክ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (አካታች ትምህርት ቤት) ገብታ እስከ 12 ኛ ክፍል እዚያ ተማረች። በትምህርት ቤቱ ካላት አካዳሚክ ተሳትፎ በተጨማሪ የተማሪዎችን አማካሪ ጨምሮ ከ 6 በላይ የክለቦችን ክበባት መርታለች ፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን በመቀላቀል የመጀመሪያ ዲግሪ በሕግ ሁለተኛ ዲግሪ በማኅበራዊ ሥራ አግኝ ታለች፡፡ ከመደበኛ ትምህርት ውጭ በልዩ ልዩ እንቅስቃሴዎች ውስጥ በተከታታይ ትሳተፋለች በዚህም የመኢአድ የፀረ ኤድስ እንቅስቃሴን ከ2004 - 05 በመምራት በ 2006 የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ (አአዩ) ሴት ተማሪዎች ማህበርን በመመስረት እንዲሁም የማህበሩ የመጀመሪያ ፕሬዝዳንት በመሆን አገልግላለች ፡፡
ለሴት ልጆች ትምህርትን አጥብቃ በመስራቷ እ.ኤ.አ. በ 2003 በደቡብ አፍሪካ የተቀበለችውን የአማኒታሪ ሽልማትን (አፍሪካዊ አጋርነት ለወሲባዊ እና ስነተዋልዶ ጤና እና የሴቶች መብቶች ) ጨምሮ ለፀረ-ኤድስ እንቅስቃሴ ባገለገለችበት ወቅት በርካታ ብሔራዊ እና ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን አግኝታለች ። ፡፡ ወ / ሮ የትነበርሽ ከአካዳሚክ ህይወቷ ባሻገር በበጎፈቃደኝነት ከ 20 በላይ ድርጅቶች ውስጥ ያገለገለች ሲሆን ከነዚህም ውስጥ በኢትዮጵያ ዓይነ ስውራን የሴቶች ክንፍ ማህበር ለ 4 ዓመታት (እ.ኤ.አ. ከ 2003 እስከ 2007) መርታለች ፡፡ ከዚያም በመቀጠል የአካል ጉዳተኞች ኢኮኖሚያዊ መብትን ጨምሮ በተለያዩ የልማት መርሃ ግብሮች ውስጥ እንዲካተቱ ለማበረታታት የኢትዮጵያ የአካል ጉዳተኞችና የልማት ማዕከል (ኢ.ሲ.ዲ.ዲ.) የተባለ አገር በቀል ድርጅት ለማቋቋም ወሰነች ፡፡ከ2016 ጀምሮ ደግሞ ቀደም ሲል በዓለምአቀፍ አምባሳደሮች ቦርድ አባልነት ወክላው ከነበረው የአካል ጉዳተኞች እና ልማት ብርሃን ለኣለም መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ጋር በመተባበር ላይ ትሰራለች ፡
የትነበርሽ ንጉሴ" የአካል ጉዳተኞችን መብትና ማካተት በማስተዋወቋ እና ሙሉ አቅማቸውን እንዲገነዘቡ የሚያስችላቸው አነቃቂ ሥራ በመስራት በማህበረሰቡ ውስጥ የአስተሳሰብ ለውጥ በመፍጠሯ" እ.ኤ.አ. በመስከረም ወር 2017 ላይ የተባበሩት መንግስታት ራይት ላይቭሊሁድ ኣዋርድ ፣ “አማራጭ የኖቤል ሽልማት” ፡ ". ክብሩን ከKhadija Ismayilova, Colin Gonsalves, እና የአሜሪካ የአካባቢ ጠበቃRobert Bilott. ጋር በመጋራት ተሸላሚ ሆናለች።ራይት ላይቭሊሁድ ኣዋርድን በማሸነፏ እና በሄለን ኬለር ሽልማት መንፈስ የተበረታታችው የትነበርሽ ንጉሴ በህይወታቸው እና በስራ መስካቸው ታላቅ ውጤት ያስመዘገቡ የአካል ጉዳተኛ ሴቶችን ለማክበር ከብርሃን ለኣለም ጋር በመሆን ‹የእርሷ ችሎታዎች ሽልማትን› ኣስጀምራለች ፡፡ www.her-abilities-award.org
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article የትነበርሽ ንጉሴ, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.