የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት

የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት በአውሮፓ አገሮች መኻል ከ ፲፱፻፮ ዓ/ም እስከ ፲፱፻፲፩ ዓ/ም መግቢያ፣ ለአራት ዓመታት የተካሄደ ጦርነት ነው። ይኼ ግጭት የዘመኑ ኃያላን አገራት በሁለት ተቃራኒ ወገን ተሰልፈው ያካሄዱት ግብግብ ሲሆን እስከ ሰባ ሚሊዮን ታጣቂዎች የተካፈሉበትና እስከ አስራ አምስት ሚሊዮን አውሮፓውያን ሕይወታቸውን ያጡበት ትልቅ ጦርነት ነው።

የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት
የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት
የጦርነቱ ታሪክ በካርታ
ቀን ከሐምሌ ፳፩ ቀን ፲፱፻፮ እስከ ኅዳር ፪ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓ.ም.
ቬርሳይ ውል የተፈረመው ሰኔ ፳፩ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓ.ም.
ቦታ አውሮፓ፣ አፍሪካ፣ መካከለኛው ምሥራቅ፣ የፓሲፊክ ደሴቶች፣ ቻይና እና ከደቡብ አሜሪካ ጠረፍ አካባቢ
ውጤት የአላይድ /allied/ ሀገሮች ድል
  • የአለማኛ፣ ሩሲያ፣ ኦቶማን እና አውስትሪያ ሀንጋሪ መንግሥታት መውደቅ
  • አዲስ ሀገራት በአውሮፓና መካከለኛው ምሥራቅ ተመሠረቱ
  • የአለማኛ ቅኝ ግዛቶችና የኦቶማን ክልሎች ወደ ሌሎች ሀገራት ተላለፉ
  • የዓለም መንግሥታት ማኅበር ተቋቋመ
ወገኖች
አላይድ ሀገራት

ፈረንሣይ ፈረንሣይ
የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ብሪታንያ
የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት የሩሲያ መንግሥት (1914–17 እ.ኤ.አ.)
የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት አሜሪካ (1917–18 እ.ኤ.አ.)
የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ጣሊያን (1915–18 እ.ኤ.አ.)
የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ጃፓን
የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ቤልጅግ
የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ሰርቢያ
የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ሮማንያ (1916–18 እ.ኤ.አ.)
የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ግሪክ (1917–18 እ.ኤ.አ.)
ፖርቱጋል ፖርቱጋል (1916–18 እ.ኤ.አ.)
የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ሞንቴኔግሮ (1914–16 እ.ኤ.አ.)
የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ብራዚል (1917–18 እ.ኤ.አ.)
እና ሌሎችም

መካከለኛው ኃያላት /central powers/

የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት የጀርመን መንግሥት
የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት አውስትሪያ ሀንጋሪ
የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት የኦቶማን መንግሥት
የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ቡልጋሪያ (1915–18 እ.ኤ.አ.)

መሪዎች
ፈረንሣይ ሬይመንድ ፑዋንካሬ

ፈረንሣይ ጊዮርጊስ ክሌሜንኮ
ፈረንሣይ ፈርዲናንድ ፎሽ
የብሪታንያ መንግሥት ኧርበርት ሄንሪ አስክዊዝ
የብሪታንያ መንግሥት ዴቪድ ሎይድ ጆርጅ
የሩሲያ መንግሥት ኒኮላይ ፪ኛ
የጣሊያን መንግሥት (1861–1946 እ.ኤ.አ.) አንቶንዮ ሳላንድራ
የጣሊያን መንግሥት (1861–1946 እ.ኤ.አ.) ቪቶሪዮ ኢማኑኤል ኦርላንዶ
አሜሪካ ዉድሮው ዊልሰን
እና ሌሎችም

የጀርመን መንግሥት ዊልሄልም ፪ኛ

የጀርመን መንግሥት ፖል ቮን ሂንደንበርግ
የጀርመን መንግሥት ኤሪክ ሉደንዶርፍ
አውስትሪያ ሀንጋሪ ፍራንዝ ጆሴፍ
አውስትሪያ ሀንጋሪ ካርል ፩ኛ
የኦቶማን መንግሥት ኢስማኤል ኤንቨር
የቡልጋሪያ መንግሥት ፈርዲናንድ ፩ኛ
እና ሌሎችም

አቅም
የሩሲያ መንግሥት 12,000,000

የብሪታንያ መንግሥት 8,841,541
ፈረንሣይ 8,660,000
የጣሊያን መንግሥት (1861–1946 እ.ኤ.አ.) 5,093,140
አሜሪካ 4,743,826
የሮማንያ መንግሥት 1,234,000
የጃፓን መንግሥት 800,000
የሰርቢያ መንግሥት 707,343
ቤልጅግ 380,000
የግሪክ መንግሥት 250,000
ፖርቱጋል 200,000
የሞንቴኔግሮ መንግሥት 50,000
ጠቅላላ፦ 42,959,850

የጀርመን መንግሥት 13,250,000

አውስትሪያ ሀንጋሪ 7,800,000
የኦቶማን መንግሥት 2,998,321
የቡልጋሪያ መንግሥት 1,200,000
ጠቅላላ፦ 25,248,321

የደረሰው ጉዳት
የሞቱ፦
5,525,000
የቆሰሉ፦
12,831,500
የጠፉ፦
4,121,000
ጠቅላላ፦
22,477,500
የሞቱ፦
4,386,000
የቆሰሉ፦
8,388,000
የጠፉ፦
3,629,000
ጠቅላላ፦
16,403,000

መነሻ

ለጦርነቱ ቅስቀሳ ብዙ ምክንያቶች በታሪክ ምሑራን ይጠቀሳሉ። ዓቢይ ከሚባሉት ነገሮች ግን የወቅቱ ኃያላን መንግሥታት የውጭ ጉዳይ ተልዕኮዎች ሲሆኑ የክብሪቱ መጫሪያ ምክንያት ግን የ አውስትሪያ እና ሁንጋሪያው ዘውድ አልጋወራሽአውስትሪያዊው አርች ዱክ ፍራንዝ ፈርዲናንድ በዩጎዝላቪያዊ ነፍሰ ገዳይ እጅ ሰኔ ፳፩ ቀን ፲፱፻፮ ዓ/ም መገደል ነው። የሳቸውን መገደል ምክንያት በማድረግ የ አውስትሪያ እና ሁንጋሪያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ለ ሰርቢያ ንጉዛት ሊያሟሉት የማይችሉትን፣ አስር ነጥብ ያዘለ የእላፊ ገደብ (ultimatum) ማስጠንቀቂያ ይሰጡና ገደቡ ሲያልፍ ቅድሚያውን እንደወጠኑት በሰርቢያ ላይ የጦር አዋጅ አወጁ። ይሄም የታቀደ ትንኮሳ ከአስር ዓመታት በፊት ተመሥርተው የነበሩትን ብዙ የትብብር ውሎችን የሚያንቀሳቅስ ሁኔታ ስለነበረ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ሁሉንም ኃያላን መንግሥታት ጦርነቱ ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ አስገደዳቸው። እያንዳንዳቸው ደግሞ በዓለም ዙሪያ የሚያስተዳድሯቸው ቅኝ ግዛቶች ስለነበሯቸው እነዚህንም ቅኝ ግዛቶች በዚሁ ግብግብ ተሳታፊ አደረጋቸው።

የጦርነቱ መግቢያ

የጦርነቱ ትርዒት የተከፈተው የአውስትሪያ እና ሁንጋሪያ ሠራዊት ሰርቢያን ሲወሩ አጋራቸው የአለማኛ መንግሥት ደግሞ ቤልጂግን፣ ሉክሳምቡርግን እና ፈረንሳይን ወረረ። በተቃራኒው ደግሞ የሩሲያ ሠራዊት የምዕራብ አለማኛን ግዛት ይወራሉ። የኦቶማን ንጉሠ ነገሥት ሠራዊት ደግሞ ወዲያው ጦርነቱ ውስጥ ሲገባ በቀጣዩ ዓመት ኢጣልያቡልጋሪያ ተከትለው ገቡበት። የሩሲያ ሠራዊት ለሦስት ዓመታት ከተዋጋ በኋላ የጥቅምት አብዮት በ፲፱፻፲ ዓ/ም ሲፈነዳ ከዚህ ታላቅ ጦርነት ወጣ።

መጨረሻው

አለማኛ ሠራዊት በ፲፱፻፻፲ ዓ/ም የምዕራብ የጦርነቱን ግንባር ማጥቃት ከጀመሩ በኋላ የአሜሪካ ሠራዊት ከአጋሮቹ ጋር ሲሰለፍ፣ የምዕራብ አገሮች ቡድን አለማኞቹን በማጥቃት እያቸነፏቸው መጡ። መጨረሻ ላይ ተሸናፊው የአለማኛ ሠራዊት መሸነፉን አምኖ ኅዳር ፩ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓ/ም የእጅ መስጫ ውል ሲፈርም፤ ሰኔ ፲፱ ቀን ፲፱፻፮ ዓ/ም የተለኮሰው ጦርነት አከተመ። አብሮትም የአውስትሪያ እና ሁንጋሪያ ግዛት፣ የኦቶማን ግዛት ሲጠፉ የጀርመን እና የሩሲያ ኃያልነት በፖለቲካም ሆነ በጉልበት ተደምስሰው የአራቱንም ቅኝ ግዛቶች አሸናፊዎቹ እንግሊዝ እና ፈረንሳይ ተከፋፈሏቸው።

የአንደኛው ዓለም ጦርነት ተስቦ

የቀድሞ ኃያላን መንግሥታትትን ውድመት ያስከተለ ክስተት ከመሆኑም ሌላ፤ በመካከለኛ አውሮፓ የብዙ ትናንሽ ሉዓላዊ አገሮችን መወለድ፤ የዓለም መንግሥታት ማኅበርን መቋቋሚያ መንስዔ፤ ከሁሉም በላይ ግን በአውሮፓ አኅጉር የብሔራዊነትን መንፈስ የቀሰቀሰና የጀርመን ሽንፈትን ያረጋገጠው የቬርሳይ ውል (Treaty of Versailles) በጀርመኖች ላይ ያስከተለው የጭቆና ስሜት አገራችን ኢትዮጵያ፲፱፻፳፰ ዓ/ም በፋሽስት ኢጣልያ በግፍ ስትወረር የተለኮሰውን የሁለተኛው የዓለም ጦርነት መነሻ ምክንያት መሆኑ ነው።

ዋቢ ምንጮች

የውጭ መያያዣ

የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት 
በ"Wiki Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለ የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።

Tags:

የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት መነሻየመጀመሪያው የዓለም ጦርነት የጦርነቱ መግቢያየመጀመሪያው የዓለም ጦርነት መጨረሻውየመጀመሪያው የዓለም ጦርነት የአንደኛው ዓለም ጦርነት ተስቦየመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ዋቢ ምንጮችየመጀመሪያው የዓለም ጦርነት የውጭ መያያዣየመጀመሪያው የዓለም ጦርነትአውሮፓ

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

ሰምና ፈትልኢያሱ ፭ኛኢትዮጵያዩ ቱብአዲስ አበባንጉሥፖልኛአሜሪካጴንጤእግዚአብሔርይስማዕከ ወርቁኮምፒዩተርየጋብቻ ሥነ-ስርዓትፍልስጤምርዕዮተ ዓለምሴቶችየጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳልየጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበርማሞ ውድነህማርችመርካቶሶፍ-ዑመርየአፍሪቃ አንድነት ድርጅትጌዴኦየኖህ መርከብኢትዮ ቴሌኮምየተፈጥሮ ሀብቶችየኢትዮጵያ ብርጥሩነሽ ዲባባሀይቅገብረ መስቀል ላሊበላሳዑዲ አረቢያክሌዮፓትራመጽሐፈ ሄኖክእየሩሳሌምዓፄ ዘርአ ያዕቆብድሬዳዋዓረፍተ-ነገርቁስ አካላዊነትክብቅዱስ ጊዮርጊስ (ሰማዕት)የኢትዮጵያ ሕገ መንግስትጋብቻየኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክጨውአዕምሮበርበሬየኢትዮጵያ ሙዚቃፋኖየጢያ ትክል ድንጋይጨለማተሳቢ እንስሳኩሽ (የካም ልጅ)የብርሃን ስብረትማርስጣናቼልሲአስቴር አወቀስቅለት (የማይክል አንጄሎ ቅርጽ)ግድግዳአብርሀም ሊንከንዋሽንትአንዶራቅፅልየካ ክፍለ ከተማሄሮዶቶስትዝታየማርቆስ ወንጌልፍቅር1200 እ.ኤ.አ.ጥር 18የኢትዮጵያ ነገሥታትቶንጋ🡆 More