አስቴር የኢትዮጵያ ታዋቂ ዘፋኝ ስትሆን ብዙ የሙዚቃ ስራዎችን ከ70ወቹ ጀምራ በማቅረብ ትታወቃለች። አስቴር ከ13 ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በወጣትነቷ ሙዚቃን ኮንቲኔንታል ባንድ፣ ሆቴል ዲአፍሪክ ባንድ፣ አይቤክስ ባንድ እና ሸበሌ ባንዶች ጋር የተለያዩ ዝግጅቶችን አቅርባለች። ከእዚያም በዝነኛው አሊ ታንጎ እገዛ ከባንድ ወጥታ በራሷ መዝፈን የጀመረችው አስቴር አወቀ ነጠላ በተለይ ከውብሸት ፍስሃ ጋር በመሆን ነጠላ ዜማዎችን በታንጎ ሙዚቃ ቤት አከፋፋይነት ለሕዝቡ ማድረስ ጀመረች። ዘጠኝ የተለያዩ ካሴቶችን ለአድማጭ ያቀረበችው አስቴር ሙናዬ የተሰኘ የመጨረሻ ካሴቷን ካሳተመች በኋላ ወደ አሜሪካ አቀናች።
አስቴር አወቀ | |
---|---|
መረጃ | |
የተወለዱት | 1953 ዓ.ም. |
የሥራ ዘመን | ከ1960ዎቹ ጀምሮ |
አስቴር አወቀ በሶዶ ክስታኔ ምድር በ፲፱፻፶፫ ዓ.ም. ተወለደች ።
1.በመልኬ አትውደደኝ 2.ፀባይህ ነው 3.ፍቅር የሚያብበው 4.የሀገሬ ትዝታ 5.ጨረቃ ውበትሽ 6.አያችሁት ወይ 7.ሽር ሽር 8.ጉብል ዓይናማ 9.ፍቅር ነው ሀብታችን
1.ሙዚቃ 2.የሸበሉ ወጣት 3.ሰላምታ 4.ብዙ አለሜ 5.ብርዱ አልተስማማኝም 6.ምነው ባይህ 7.እኔ ቀጥሮ እለኝ 8.ና አካሌ
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article አስቴር አወቀ, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.