ቶጎ የምዕራብ አፍሪካ ሀገር ነው። ይፋዊ ብሔራዊ ቋንቋ ፈረንሳይኛ ሲሆን ከ39 ኗሪ ቋንቋዎች በላይ ይገኛሉ። ከነዚህም ሁለቱ ኤዌኛ እና ካቢዬኛ እንደ አገራዊ ልሳናት ዕውቅና ተቀብለዋል።
የቶጎ ሪፐብሊክ | ||||||
---|---|---|---|---|---|---|
| ||||||
ብሔራዊ መዝሙር: Salut à toi, pays de nos aïeux | ||||||
ቶጎ በቀይ ቀለም | ||||||
ዋና ከተማ | ሎሜ | |||||
ብሔራዊ ቋንቋዎች | ፈረንሳይኛ | |||||
መንግሥት ፕሬዚዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር | ሪፐብሊክ ፋውረ ግናሲንግቤ ኮሚ ሴሎም ክላሱ | |||||
ዋና ቀናት ሚያዝያ ፲፱ ቀን [1952 | የነፃነት ቀን ከፈረንሣይ | |||||
የመሬት ስፋት አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.) ውሀ (%) | 56,785 (125ኛ) 4.23 | |||||
የሕዝብ ብዛት የ2017 እ.ኤ.አ. ግምት የ2010 እ.ኤ.አ. ቆጠራ | 7,178,000 (101ኛ) 5,337,000 | |||||
ገንዘብ | CFA ፍራንክ | |||||
የሰዓት ክልል | UTC +0 | |||||
የስልክ መግቢያ | +228 | |||||
ከፍተኛ ደረጃ ከባቢ | .tg |
ከኗሪዎቹ 51% ያህል የባህላዊ አረመኔነት ተከታዮች ናቸው፤ 29% ያህል የክርስትና፣ 20% ያሕል የእስልምና አማኞች ናቸው። የባህላዊ ተከታዮቹ ብዙ የእጅ ሥራዎች፣ የጣኦት ምስል፣ ስጋጃ፣ የወገብ ጨርቅ፣ ሌላ ሥነ ጥበብ ይፈጥራሉ። ብሔራዊ መጠጡ ሶዳቢ ወይም የኮኮነት ዘምባባ አረቄ ይባላል። ከሁሉ የተወደደ እስፖርት እግር ኳስ ሲሆን ብሔራዊ የቅርንጫት ኳስ ቡድን ደግሞ አለ።
ወደ ውጭ አገር የሚላኩ ሸቀጦች በተለይ ካካው፣ ቡና፣ ጥጥ፣ ፎስፌት፣ ኦቾሎኒ፣ ሲሚንቶ ናቸው።
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ቶጎ, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.