ታይላንድ በደቡብ-ምሥራቅ እስያ በአውሮፓ አገራት መቸም ያልተገዛው ብቸኛ አገር ነው። ዋና ከተማው ባንኮክ ነው። እስከ 1931 ዓ.ም፣.
ድረስና እንደገና ከ1937 እስከ 1941 ዓ.ም. ድረስ የአገሩ ስም በይፋ ሳያም ነበረ።
የታይላንድ መንግሥት | ||||||
---|---|---|---|---|---|---|
| ||||||
ታይላንድ በአረንጓዴ ቀለም | ||||||
ዋና ከተማ | ባንኮክ | |||||
ብሔራዊ ቋንቋዎች | ጣይኛ | |||||
መንግሥት ንጉሥ ጠቅላይ ሚኒስትር | ማሃ ዋጪራሎንግኮን ፕራዩት ጫንዖጫ | |||||
የመሬት ስፋት አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.) ውሀ (%) | 513,120 (51ኛ) 0.4 | |||||
የሕዝብ ብዛት የ2011 እ.ኤ.አ. ግምት የ2000 እ.ኤ.አ. ቆጠራ | 66,720,153 (19ኛ) 66,720,153 | |||||
ገንዘብ | ባት (฿) | |||||
የሰዓት ክልል | UTC +7 | |||||
የስልክ መግቢያ | +68 | |||||
ከፍተኛ ደረጃ ከባቢ | .th እና .ไทย |
የታይላንድ መንግሥት ሃይማኖት ቡዲስም ነው።
የታይላንድ ባህል ምግብ እጅግ የተቀመመ ነው፣ አበሳሰሉም በተለይ ስኳር፣ ፍራፍሬ፣ ሚጥሚጣ፣ አሣ ይጠቅማል። ከሁሉ የተወደደ እስፖርት እግር ኳስ ነው፤ ሆኖም ታክራው የሚባል ሌላ ኗሪ የኳስ ጨዋታ ይወደዳል። ታይላንድ «የፈገግታ አገር» በመባል ታውቋል፤ በጣም ጨዋ አገር ነው፤ ሰላምታ ሲሰጡም ፈገግ ማለት እና መዳፎች አንድላይ በማድረግ እጅ መንሣት አይነተኛ ነው።
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ታይላንድ, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.