ቢግ ማክ የሃምበርገር ዓይነት ሲሆን በፈጣን ምግብ ቤቱ ማክዶናልድስ የሚሸጥ ነው። ሃምበርገሩ ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈጠረው በ1960 ዓ.ም.
በአሜሪካዊው ጅም ዴልጋቲ ነበር። ሁለት የተፈጨ የበሬ ስጋ ክቦችን፣ ሰላጣ ቅጠል፣ ዓይብ፣ ሽንኩርት፣ ፒክልስ እና ሶስት የሰሊጥ ጠፍጣፋ ዳቦዎችን ከማዋዣ የቢግ ማክ ሶስ (መረቅ) ጋር ይይዛል።
ቢግ ማክ በአሁኑ ዘመን በአለም ዓቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተወዳጅነት በማግኘቱ ዘ ኢኮኖሚስት የተሰኘው የሥነ ንዋይ ጋዜጣ በያመቱ ቢግ ማክ ኤንዴክስ የተባለ መረጃ ያትማል። ቢግ ማክ በያገሩ የሚሸጥበትን ዋጋ በማዎዳደር፣ የየአገሩን የኑሮ ውድነት ለማነጻጻር ይጠቀምበታል።
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ቢግ ማክ, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.