ኅብረተሰብ

ሥነ ሕብረተሰብ


ሥነ ሕብረተሰብ የሰው ልጆች በቡድንና በተናጥል ያላቸውን ጠባይና አደረጃጀት የሚያጠና ክፍል ነው።

ኅብረተሰብ
የዕለቱ ምርጥ ጽሑፍ

ለሴ ፈር


ለሴ ፈር (ፈረንሳይኛ laissez-faire «ያድርጉ» ወይም ቃል በቃል «ለማድረግ ፍቀዱ») ማለት ባለሥልጣናት በግለሠቦች መገበያየት ጥልቅ ሳይገቡ ቀርተው (ግፍ ወይም ሥርቆት ከመከልከል በቀር) የሚታገሡበት የምጣኔ ሀብት ዘዴ ነው።

በፈረንሳይኛ ዘይቤው «ለሴ ፈር» ከ1671 ዓም ጀምሮ እንዲታወቅ ይታመናል። ፍልስፍናው ከፈረንሳይ ይልቅ በታላቁ ብሪታን እንዲሁም በአውሮፓና በአሜሪካ ውስጥ ዘመናዊ ሆነ። በጥንቱ ቻይና ደግሞ ተመሳሳይ የአገዛዝ ፍልስፍና «ዉ ወይ» («ያለመሥራት») ይታወቅ ነበር። በለሴ ፈር ምክንያት የአውሮፓና የአሜሪካ ምጣኔ ሀብትና ንግድ ድርጅቶች ሊያብቡ እንደ ቻሉ፣ በፋብሪካ አብዮት በኩል ኑሮ ዘዴ እንዲለወጥና እንዲቀለል፣ አዳዲስ መጓጓዣና መገናኛ ፈጠራዎች እንዲገኙ ያስቻለው ሁሉ ይታመናል።

የፈጠራዎች ታሪክ ስንመለከት፣ ከ200 ዓክልበ. እስከ 1200 ዓም ያህል አብዛኞቹ አዳዲስ ፈጠራዎች የተደረጁ ከቻይና ነበረ፤ ወይም እስከ ሞንጎሎች ግዛት ድረስ። እንዲሁም ከ1500 እስከ 1940 ዓም ያሕል አብዛኞቹ አዳዲስ ፈጠራዎች የተደረጁ በምዕራባውያን አለም ነበረ። ....

ኅብረተሰብ
የዕለቱ ምርጥ ምስል

ቢግ ማክ


ኅብረተሰብ
ቢግ ማክ

ቢግ ማክ የሃምበርገር ዓይነት ሲሆን በፈጣን ምግብ ቤቱ ማክዶናልድስ የሚሸጥ ነው። ሃምበርገሩ ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈጠረው በ1960 ዓ.ም. በአሜሪካኑ ጅም ዴልጋቲ ነበር። ሁለት የተፈጨ የበሬ ስጋ ክቦችን፣ ሰላጣ ቅጠል፣ ዓይብ፣ ሽንኩርት፣ ፒክልስ እና ሶስት የሰሊጥ ጠፍጣፋ ዳቦዎችን ከማዋዣ የቢግ ማክ ሶስ (መረቅ) ጋር ይይዛል።

ቢግ ማክ በኣሁኑ ዘመን በአለም ዓቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተዎዳጅነትን በማግኘቱ ዘ ኢኮኖሚስት የተሰኘው የሥነ ንዋይ ጋዜጣ በያመቱ ቢግ ማክ ኤንዴክስ የተባለ መረጃ ያትማል። ቢግ ማክ በያገሩ የሚሸጥበትን ዋጋ በማዎዳደር፣ የየአገሩን የኑሮ ውድነት ለማነጻጻር ይጠቀምበታል።

ኅብረተሰብ
የዕለቱ ምርጥ የሕግ ጽሑፍ

ህግ ተርጓሚ


ህግ ተርጓሚ ወይም ፍርድ ቤት፡ ፍርድ የመስጠት ስልጣን ያለው የመንግስት አካል ነው። ከሶስቱ ከፍተኛ የመንግስት አካላት ማለትም ህግ አውጭ፣ ህግ ተርጓሚ እና ህግ አስፈጻሚ አንዱ ነው። ይህ አካል ህግ ተርጓሚ የሚባለው ነው። የወንጀለኛ መቅጫ ህግ፣ ሲቪል ህግ፣ አስተዳደራዊ ህግ እና ሌሎች ህጎችን በ የህግ የበላይነት ላይ መሰረት በማድረግ ይተረጉማል።

ታሪክ

ፍርድ በኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ ታሪክ ያለው ክንውን ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ በተለምዶ ወይም ባህል በበላ ልበልሃ እየታገዘ በመንደር ሽማግሌዎች ወይም በሀገረ ገዥዎች ፊት ይቀርብ ነበር። ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አገዛዝ ወዲህ በዘመናዊው የመንግስት መዋቅር የህግ ተርጓሚነትን የመንግስት ሰልጣን ተሰጥቶት መንግስት በሾማቸው ዳኞች ይመራል።

ገለልተኝነት

ይህ አካል በዘመናዊዉ የዴሞክራሲ መርህ ከየትኞቹም የመንግስት አካላት በገለልተኝነት ይንቀሳቀሳል። ሶስቱም የመንግስት አካላት ጣልቃ መግባት አይችሉም። በሃገሪቱ የሚገን ማንኛውም ዜጋ፣ አካል፣ ወይንም ተቋም ይዳኝበታል።

ኅብረተሰብ
የዕለቱ ምርጥ የፖለቲካ ጽሑፍ

ዴሞክራሲ


ዴሞክራሲ የፖለቲካ ሥርዓት ሲሆን ትርጓሜውም ሕዝባዊ መንግስት ማለት ነው። በሌላ አባባል ዲሞክራሲ ማለት ህዝብ የሚያስተዳድረውን አካል ያለምንም ተፅዕኖ ከመካከሉ መርጦ ሥልጣን የሚሰጥበት ሥርዓት ነው።

ኅብረተሰብ
የዲሞክራሲ መጠን በያገሩ (2009 ዓ.ም. )
*ሰማያዊ -- በጣም ዲሞክራሲያዊ (ዎደ 10 የተጠጋ
*ጥቁር -- ትንሽ ዲሞክራሲያዊ (ዎደ 0 የተጠጋ)
  • ዴሞክራሲ ለምን ተፈለገ?

እንደ ፈላስፋው ጆን ስቱዋርት ሚል ሦስት ምክንያቶች ይጠቀሳሉ፦

    • ሥልታዊ ምክንያት

ሕግ አርቃቂዎች ለአንድ ሕብረተሰብ ጥቅም፣ መብት እና አስተሳሰብ ትኩረት እንዲሰጡ ከሌሎች የፖለቲካ ሥር ዓቶች በላይ ዴሞክራሲ ያስገድዳቸዋል። ስለዚህ ሰዎች በሥርዓቱ ውስጥ የመጎዳታቸው ዕድል አንስተኛ ነው። ተመራማሪ ዓማርትያ ሴን ዋቢ ሲሰጥ «በ[ታሪክ ውስጥ ] በማናቸውም ሉዓላዊ ዲሞክራሲያዊ መንግስታት ከፍተኛ ርሃብ ተከስቶ አያቅም» ይላል። ፖሊሲ አውጭዎች ለሕዝብ ተገዥ ስለሆኑ።

ዴሞክራሲ አብዛኛውን ሕዝብ በውሳኔ አስጣጥ ላይ ስለሚያካፍል፣ ከሌሎች የፓለቲካ ሥርዓቶች በበለጠ የዜጎችን ጉዳይ ያዎቀ ሆኖ ይገኛል። በውሳኔ አሰጣጥ የሚካፈለው ሕዝብ መብዛት በሌላ ጎን ትክክለኛ ውሳኔ ላይ ለመድረስ እሚደረገውን ስራ ያግዛል፣ ተሳታፊዎችም ስለ ጉዳዮች የበለጠ የተተቸና የተብራራ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ይረዳል።

    • የዜጎችን ባሕርይ የማሻሻል ምክንያት

በዴሞክራሲ ሥርዓት ያሉ ሰዎች በውሳኔዎች ላይ ስለሚሳተፉ፤ ከሌሎች ሥርዓት ሰዎች በተለየ እራሳቸውን ችለው እንዲያስቡ፣ በሃሳባቸው ምክኑያዊ እንዲሆኑ እና የሌሎችን መብቶች ግምት ውስጥ እንዲያስገቡ ስለሚገደዱ በሥነ ምግባር እንዲሻሻሉ ይሆናሉ።

ዴሞክራሲ ከሚያስከትለው ጥቅም ውጭ በጥቅመኝነት የማይገኙ ሌሎች ሥነ ምግባራዊ ምክንያቶችይጠቀሳሉ። ለምሳሌ ሓርነት ፣ ዕኩልነት፣ የሕግ የበላይነት፣ የመናገር መብት፣ ፍትህ ይጠቀሳሉ

ኅብረተሰብ
የዕለቱ የኢኮኖሚ ምርጥ ጽሑፍ

ገንዘብ

ኅብረተሰብ
ሳንቲም እና ብር – በብዛት በስራ ላይ በተጨባጩ አለም ውስጥ የተሰማሩ የገንዘብ አይነቶች ናቸው። ገንዘብ ከነዚህ ውጭ ሊሆን ይቻላል።

በአንድ አገር ወይም ማህበረሰብ ውስጥ ለሸቀጥ (አሰፈላጊ እቃ) ና አገልግሎት መግዢያ እንዲሁም እዳ መክፈያ የሚያገለግ ማንኛውም ነገር ሁሉ ገንዘብ ይባላል።

የጥንቱ ገንዘብ ዋጋ ይመነጭ የነበረው ከራሱ ከተሰራበት እቃ ዋጋ ነበር (ለምሳሌ፡ ከወርቅ የተሰራ ሳንቲም) ። በዚህ ምክንያት እንዲህ አይነቱ ገንዘብ የኮሞዲቲ ገንዘብ ይባላል። በአሁኑ በአለማችን የሚሰራባቸው ገንዘቦች በራሳቸው የራሳቸው የሆነ ዋጋ የላቸውም (ለምሳሌ ከተልባ እግር የተሰራው ዶላር በራሱ ዋጋ የለውም) ። ይህ አይነት ገንዘብ ፊያት ገንዘብ ሲባል ዋጋው የሚመነጨው የአንድ አገር መንግስት ህጋዊ መገበባያ ብሎ ስላወጀው ብቻ ነው። ህጋዊ መገበባያ ሲባል ለማንኛውም በዚያ አገር ውስጥ ላለ እዳ ይህ የታወጀው ገንዘብ እንደ ክፍያ ሲቀርብ "አይ! አልቀበልም" ማለት ክልክል ነው። በዚህ ምክንይት የፊያት ገንዘብ ዋጋ ከመንግስት ሃይል ጋር ከፍተኛ ግንኙነት አለው።

ያንድ ዘመናዊ ሃገር የገንዘብ አቅርቦት በሁለት ይከፈላል፣ ይኸውም ተጨባጭ የሆነው የታተመው ብርና በማይጨበጥ መልኩ በባንክ ቤት ተጠራቅሞ ያለው በቼኪንግ እና ሴቪንግ የሚከፈለው የባንክ ሒሳብ ነው። ባብዛኛው ጊዜ እኒህ የ ባንክ ሒሳቦች ታትሞ ከቀረበው ብር በላይ ናቸው። በምናባዊ አለም ውስጥ የተቀመጡት እነዚህ የቁጥር ሰነዶች ምንም እንኳ የማይታዩና የማይዳሰሱ ቢሆንም ልክ እንደ ጥሬ ብር እኩል ለመሸጥና ለመለወጥ ያገለግላሉ። ...

ኅብረተሰብኅብረተሰብኅብረተሰብኅብረተሰብኅብረተሰብኅብረተሰብኅብረተሰብኅብረተሰብኅብረተሰብኅብረተሰብኅብረተሰብኅብረተሰብኅብረተሰብኅብረተሰብኅብረተሰብኅብረተሰብ
  መደቦች
ኅብረተሰብ
ፓለቲካ
ኅብረተሰብ
ኢኮኖሚ (ሥነ ንዋይ)
  • የኢኮኖሚ ሥርዓቶች (መደብ): የገበያ ኢኮኖሚ  የታቀደ ኢኮኖሚ  ቅይጥ ኢኮኖሚ
  • ፋይናንስ (መደብ): ባንክ (መደብ)  ሼር(ድርሻ) (መደብ)  ደርቬቲቭ (መደብ)  ፈንድ (መደብ)  ቦንድ (መደብ)
  • አለም አቀፍ ኢኮኖሚ (መደብ): እርዳታ (መደብ)  ግሎባላይዜሽን (አለም አቀፋዊነት) (መደብ)  ነጻ ንግድ
  • ቢዝነስ (መደብ) ኩባንያ (መደብ)  ቢዝነስ (መደብ)  ንግድ (መደብ)
ኅብረተሰብ
ሕግ
  • አለም አቀፍ ሕግ (መደብ): ስምምነት (መደብ)  ሰብዓዊ መብት (መደብ)  የጦርነት መብት (መደብ)
  • የሕብረተሰብ ሕግ (መደብ): የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ (መደብ)  ሕገ መንግስት (መደብ)  ክስ (መደብ)
  • ፍትሐ ብሔር (መደብ): የሰራተኞች ሕግ (መደብ)  የኮንትራክት ሕግ (መደብ)  የቤተሰብ ሕግ (መደብ)  የአዕምሮ ሃብት ሕግ (መደብ)
  • ሕግ አስከባሪ (መደብ): ፍርድ ቤቶች (መደብ)  ፖሊስ (መደብ)  አመክሮ (መደብ)
ኅብረተሰብ
ትምህርት
  • ትምህርት ቤት (መደብ): ዩኒቨርሲቲ (መደብ)  አንደኛ ደረጃ  ሁለተኛ ደረጃ (መደብ)  መዋዕለ ህጻናት
  • ትምህርት (መደብ): ጥናት
ኅብረተሰብ
ሕብረተሰብ
ኅብረተሰብ
ሃይማኖት
  ተጨማሪ

ሕዝባዊ ጉዳዮች

ሕግ ሥነ ንዋይ (ኢኮኖሚክስ) የሰው ልጅ ጥናት

የባሕል ጥናት (ሶሲዮሎጂ) ትምህርት ሃይማኖት የመጻሕፍት ቤትና የመረጃ ጥናት

Tags:

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

አርጀንቲናሐምራዊክራርሸክላበ1948 ዓ.ም. ተሻሽሎ የወጣ የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥትአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስአምቦሼህ ሁሴን ጅብሪልሊጋባኦሮሚያ ክልልማህተማ ጋንዲየኢትዮጵያ ባህር ኃይልአክሊሉ ሀብተ-ወልድኅሩይ ወልደሥላሴ (ብላቴን ጌታ)ኦሮሞኢስታንቡልፈንገስኒኮላ ተስላፅጌ ማርያም ገብሩ ደስታምሳሌየተባበሩት የዓረብ ግዛቶችዶሮ ወጥህግ አውጭአሰፋ አባተእግዚአብሔርየዊኪፔዲያዎች ዝርዝርበጋፓርላማዋንዛዘጠኙ ቅዱሳንፋሲል ግምብየማርያም ቅዳሴ ገፅ ፲፩ቅዱስ ጊዮርጊስ የእግር ኳስ ቡድንሥነ ንዋይዕብራይስጥንጉሥየኖህ ልጆችእስያከነዓን (የካም ልጅ)ቱርክየተባበሩት መንግሥታት ድርጅትኖቤል ሽልማትዝንዠሮገበጣነፕቲዩንቋንቋአዳም ረታሳያት ደምሴዴሞክራሲክርስቲያኖ ሮናልዶብሉይ ኪዳንአፈርኤችአይቪጥቁር እንጨትፋሲለደስሰንበትዩ ቱብፔንስልቫኒያ ጀርመንኛወልቂጤዶዶላ (ወረዳ)ልብወለድ ታሪክ ጦቢያየሉቃስ ወንጌልኤፍሬም ታምሩሰዋስውከንባታሸዋኦሪትፍትሐ ነገሥትአፍሪቃቅዝቃዛው ጦርነትኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽንዘመነ መሳፍንትእንስሳየኢትዮጵያ እጽዋትቀነኒሳ በቀለካራማራጸሐፌ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴ ወልደ አረጋዊ🡆 More