ሳይንስ

ሳይንስ
ሳይንስ
ወደ   ሳይንስ   ክፍል   እንኳን   ደህና   መጡ!


ሳይንስ ከተጨባጩ ዓለም በሥርዓት መረጃ የሚሰበስብ፤ ከተሰበሰበው መረጃ ተነስቶ ዕውቀት የሚገነባ እና በተመክሮ ቢፈተኑ ጸንተው ሊቆሙ የሚችሉ ትንቢቶችንና ማብራሪያዎችን የሚያስገኝ የዕውቀት ዓይነት ነው።

በፍልስፍና አስገዳጅ ዕውነት (የአምክንዮ ዕውነት) እና አጋጣሚ ዕውነት (ሓቅ) የተባሉ ሁለት ዓይነት ዕውነቶች አሉ። የሳይንስ ዕውቀቶች በአጋጣሚ ዕውነቶች (ሓቆች)ላይ የተመሰረቱ ናቸው። ይህም ሲባል ለሓቆች እንዲህ ሆኖ መገኘትና፣ እንደዚያ ሆኖ አለመገኘት አስገዳጅ አመክንዮ የለም። ለምሳሌ መሬት በላይዋ ላይ ያለን ማንኛውንም ቁስ ትስባለች፣ ይህ ግን ያለንበት ዓለም ዕውነታ ነው እንጂ መሬት ማንንም ባትስብ ምንም የአመክንዮ መጣረስ አይኖርም። በሌላ አነጋገር፣ አንድ ሰው ከ ጥሩ መሪ ሃሳቦች ተነስቶ፣ በጥሩ አመክንዮ፣ «የመሬት ስበት የለም» እሚል ድምዳሜ ላይ ሊደርስ ይችላል። ድምዳሜው ስህተት መሆኑን በምንም ዓይነት በአመክንዮ ብቻ ማዎቅ አይቻልም ምክንያቱም የአመክንዮ መጣረስ ስለማይፈጥር። በአጠቃላይ መልኩ፣ ሓቆች በአዕምሮ ፍልስፍና ብቻ ሊደረስባቸው አይቻልም።

ሳይንስ በአመክንዮ ብቻ ሳይሆን በተጨባጩ አለም ውስጥ በመሞከር፣ ከተሞክሮውም ዕውነትና ውሸቱ እየጠራና እየተመዘገበ በሂደት እየተሻሻለ የሚሄድ የዕውቀት አይነት ነው። የመሬትን ስበት ሓቅነት ለመገንዘብ እሚፈልግ በማሰብ ብቻ ሳይሆን ዘሎ መሬትን ለማምለጥ በመሞከር ሊያውቅ ይችላል። ለዚህና ለመሳሰሉት ስራዎች፣ ዘመናዊው ሳይንስ የሳይንሳዊ ዘዴን ይጠቀማል።

ዘመናዊው ሳይንስ ፣ ሰፊ ዕውቀትን በመሰብሰብ ብቻ ሳይሆን ይህን ዕውቀት በሥራ ላይ በማዋል ያለተወዳዳሪ የሰውን ልጅ ህይወት በማሻሻል ላይ ይገኛል። በሽተኞች መታከማቸው፣ የእርሻ ምርት መትረፍረፍ፣ የመገናኛ ብዙሃን መፈጠርና ማደግ፣ ወዘተ...እነዚህ ሁሉ የዚህን ዕውቅት ሥኬት የሚያሳዩ ናቸው።






ሳይንስ


ጨረቃ በመሬት ከፀሐይ ስትጋረድ


ለዕለቱ የተመረጠ የሳይንስ ምስል



ለዕለቱ የተመረጠ የሳይንስ ጽሑፍ

ብርሃን


ነጭ ብርሃን የሁሉ ቀለሞች ድምር ውጤት እንደሆነ
ነጭ ብርሃን የሁሉ ቀለሞች ድምር ውጤት እንደሆነ

ብርሃን ነገሮች በዓይን እንዲታዩ የሚያደርግ የተፈጥሮ ሞገድ ነው። የብርሃን ሞገድ ከኤሌክትሪክ እና ከመግነጢስ የተሰራ ስለሆነ ሞገዱ የ ኤሌክትሮመግነጢስ ጨረራ ይባላል። ይሁንና፣ የኤሌክትሮመግነጢስ ጨረራ ብርሃንን ብቻ ሳይሆን የብርሃንን ታናናሽና ታላላቅ ወንድሞች ሳይቀር ያፈልቃል። ከብርሃን ታናናሽ ወንድሞች፣ ሬዲዮ፣ ራዳር እና ታህታይ ቀይ ይገኙበታል። ታላላቅ ወንድሞቹ ቢባል፣ ላዕላይ ወይን ጠጅ፣ ኤክስ ሬይ፣ ጋማ ጨረር ይገኛሉ። እነዚህ የብርሃን ወንድሞች በተፈጥሯቸው ከብርሃን ጋር አንድ ቢሆኑም ፣ የሰው ዓይን ሊያያቸው ስለማይችል ብርሃን አይባሉም። ሆኖም ግን አንድ አንድ እንስሳት እነዚህን ሞገዶች መመልከት ይችላላሉ። ለምሳሌ ታህታይ ቀይ የሚባለው የብርሃን ታናሽ ወንድም፣ ለሰዎች እንደ ብርሃን ሳይሆን እንደ ሙቀት ሆኖ ይሰማል። ለምሳሌ የፀሐይ መሞቅ ከምትተፋው የታህታይ ቀይ ጨረራ ይመነጫል። በበረሃ የሚንከላዎሱ እባቦች ይህን ሞገድ በአይናቸው መመልከት ስለሚችሉ፣ ሙቀት ያለውን ማንኛውንም ነገር በጭለማ ሳይቀር ማየት ይችላሉ። ንቦች በተቃራኒ፣ የሰው ልጅ እማያየውን ላዕላልይ ወይን ጠጅ ሞገድ በዓይናቸው ማየት ስለሚችሉ፣ አበቦች ለንቦች ከሰው ልጅ የተለየ መልክና መልዕክት ያስተላልፋሉ።

ብርሃን ሞገድ ብቻ ሳይሆን፣ እንደሌሎቹ ጨረራዎች የሞገድና እኑስ ሁለትዮሽተፈጥሮን አዋህዶ የያዘ ነው። ስለዚህና ስለመሳስሉት መሰረታዊ የብርሃን ባህርያት የሚያጠናው የዕውቀት ዘርፍ ሥነ ብርሃን (ኦፕቲክስ) በመባል ይታወቃል። የተፈጥሮ ህግጋት ጥናት (ፊዚክስ) ምርምር ዋና ክፍል ነው። የበለጠ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ ...

ሳይንስ
የተፈጥሮ ሕግጋት ጥናት (ፊዚክስ)
ሳይንስ
ሥነ ቅመማ (ኬሚስትሪ)
ሳይንስ
ሥነ ሕይወት (ባዮሎጂ)
ሳይንስ
  • ቅይጥ (ሚክስቸር)
    • ቅይጥ ብረት አስተኔ(አሎይስ)
  • ኢካርቦናማ ሥነ ቅመማ (ኢንኦርጋኒክ)
  • ካርቦናማ ሥነ ቅመማ (ኦርጋኒክ)
  • ተንታኝ ኬሚስትሪ(አናላይቲክ)
  • ኑክሌር ኬሚስትሪ
  • ኬሚካል ኢንጂኔሪንግ
ሥነ ሕክምና
ሳይንስ
ሥነ መሬት
ሳይንስ
ሥነ ፈለክ
ሳይንስ
ተግባራዊ ሳይንስ
ሳይንስ
  • እንስሳት ሕክምና
    • የእንስሳት በሽታዎች
  • የድመት ጤንነት
  • የውሻ ጤንነት
  • የአሳ ጤንነት



Tags:

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

ሻታውኳእስራኤልክትፎፌስቡክጌዴኦሀይቅየኢትዮጵያ ቋንቋዎችየተባበሩት ግዛቶችኢንዶኔዥያመጠነ ዙሪያእየሱስ ክርስቶስሐረሪ ሕዝብ ክልልሥነ-ፍጥረትቤተ ጎለጎታመንግሥተ አክሱምእነሞርሥልጣናዊነትጎርጎርያን ካሌንዳርNorth Northኔዘርላንድጀርመንወንጌልደቡብ አፍሪካንጉሥ1960 እ.ኤ.አ.ጋምቤላ ሕዝቦች ክልልኤርትራቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልልትንቢተ ኢሳይያስተውሳከ ግሥታሪክቤተ አባ ሊባኖስመጽሐፈ ዮዲትየኦሎምፒክ ጨዋታዎችምሥራቅሐረርሰምና ፈትልስዕልቻይንኛህሊናሽመናኦሮምኛስንዱ ገብሩአዲስ ኪዳንቋንቋራስ ጎበና ዳጨ ከ1882-1889ሚሲሲፒ ወንዝሚዳቋአሜሪካኧሸርየዮሐንስ ራዕይአውሮፕላንቀይ ተኩላየዋና ከተማዎች ዝርዝርክርስቶስኑግ ምግብአቡነ ባስልዮስቼኪንግ አካውንትዕድል ጥናትአዶልፍ ሂትለርኤፍሬም ታምሩየኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙርየዓለም፡ታሪክ፡ከፍጥረት፡ጀምሮ፡እስከ፡ዘመናችን፡ድረስ፡ 1834ዮሐንስሙቀትአዲስ ዘመን (ጋዜጣ)ቅዱስ መርቆሬዎስአፈርፋሲል ግምብ🡆 More