ሒሳብ

ሒሳብ
ወደ   ሒሳብ   ክፍል   እንኳን   ደህና   መጡ!

  ሒሳብ                   ሒሳብ                      ሒሳብ                             ሒሳብ


የሒሳብ ስራና ግንዛቤ እሚከወነው በአእምሮ እንደመሆኑ የዕውቀቱ መሰረቶች ለቂቅ ሃሳቦችና በነርሳቸውም መካከል ያለ መመሳሰል እና ልዩነት ነው። ቁጥር የሒሳብ ዕውቀት መሰረታዊ ገንዘብ ነው ፤ አመጣጡም ለምሳሌ በአራት ድንጋዮችና በአራት ወፎች መካከል አንድ የጋር ነገር እንዳለ፣ ያም ብዛታቸው እንደሆነ ከመረዳት ነው። አራትነት ለቂቅ ነው ይተባለበት ምክንያት በተጨባጭ ያለ ነገር ሳይሆን፣ አዕምሮ ከተሰጡት የማይመሳሰሉ ሁለት ዓይነት ነገሮች አላቆ ያወጣው የጋራቸው ሃሳብ መሆኑ ነው። ከቁጥር ተጨማሪ ቅርጽ ፣ አደረጃጀት፣ እና ለውጥ በሒሳብ የሚጠኑ ሌሎቹ ለቂቅ ሃሳቦች ናቸው።

አንድ የሒሳብ ጽንስ ዕውነት መሆኑ የሚረጋገጠው ከሒሳብ ውስጣዊ ስነ አመክንዮ እና ከመሪ ሃሳቦቹ አንጻር ብቻና ብቻ ነው። ስለዚህም በሒሳብ ስራ ውስጥ ለመሳተፍ አንድ ሰው ማዕረግም ሆነ ስልጣን በምንም መልኩ አያስፈልገውም። ሐቀኝነት፣ ግልጽነት፣ አዲስ የመፍጠር ፍላጎት፣ እርሳስና ወረቀት ለሒሳብ ስራ አስፈላጊና በቂ ጥሬ ዕቃዎች ናቸው።

አዳዲስ የሒሳብ ቅርንጫፎች በፍጥነት እየበቀሉ እና እየተስፋፉ ባለበት በአሁኑ ወቅት በዚያው ልክ ከዛሬ ሶስትና አራት ሺህ ዓመታት በፊት በግብጽና በባቢሎን ይሰራባቸው የነበሩ የሒሳብ ስሌቶች ያለምንም ለውጥ አሁን ድረስ ያገለግላሉ። ይሄ የሚያሳየው የዕውቀቱን አስተማማኘትና የዘዴውን ብቃት ነው።



:መደብ:ሥነ ቁጥር


ምርጥ ጽሑፍ
ትርምስ

ትርምስና ድርደራ:
ትርምስና ድርደራ:

ከዕለታት አንድ ቀን ስንዱ የተባለ ተማሪ 10 አዛምድ ጥያቄዎች ፈተና ላይ ቀረቡለት። ስንዱ እንደስሙ የሆነ ተማሪ ስላልሆነ፣ ጥያቄዎቹን ዘቅዝቆ ቢያነባቸው እንኳ ምንም ሊረዳቸው አልቻለም፤ እንዲሁ በነሲብ (እውር ድንብስ) አዛምዶ ከሁሉ በፊት ፈተናውን ጨርሶ ወጣ። ስንዱ፣ ምን አይነት ውጤት ከፈተናው ሊጠብቅ ይችላል?


ይሄ ጥያቄ ትርምስ በሚባል የሥነ ጥምረት መንገድ በቀላሉ ሊሰላ ይችላል! ሆኖም በመጀመሪያ ተማሪው አጠቃላይ ፈተናው በስንት አይነት መንገድ ሊመልስ ይችላል? የሚለውን መመለስ ግድ ይላል። በ ድርደራ ዘዴ እንዲህ ይሰላል፦ 10! = 3628800 መንገዶች! ከነዚህ ውስጥ በስንት መንገድ ሁሉንም ጥያቄ ስህተት ያገኛል? በ ትርምስ ዘዴ እንዲህ ይሰላል ፦ !10 = 1334961 መንገዶች! ስለዚህ ከ አስሩ ዜሮ የማግኘት እድሉ 1334961/3628800 = 36.79% ነው!! ከ አስሩ ፣ አንድ የማምጣት እድሉ ስንት ነው? መጀመሪያ ከአስሩ ጥያቄ ትክክለኛው አንድ ጥያቄ በስንት ይመረጣል? በምርጫ (ሒሳብ) እንዲህ ይሰላል፦ ፣ ግን ደግሞ ቀሪው ዘጠኝ ጥያቄ ስህተት መሆን ስላለበት በትርምስ እንዲህ ይሰላል፡ !9 - ስለሆነም ከአስሩ አንድ የማምጣት መንገዱ ብዛት = 1334960 ነው። ከዜሮ ከማግኛ መንገዶች በአንድ ብቻ ያንሳል። ከአስሩ ሁለት ማግኛው ብዛት ደግሞ !8* ይሆናል ማለት ነው።

ስለዚህ ተማሪው፣ ከአስሩ ዜሮ ወይንም አንድ ወይንም ሁለት የማምጣት እድሉ አጠቃላይ ሲሰላ፦ (!10 + + !8* )/ (10!) = 92% ነው ማለት ነው። በዚህ ስሌት፣ ተማሪው ከ አስሩ ሶስት፣ አራት ወይንም ከዚያ በላይ የማምጣት እድሉ 8% ብቻ ነው። ይህ ዕድል በጣም አንስተኛ ስለሆነ፣ ያልተሰናዳው ስንዱ ከ አስሩ ሁለት ወይንም ከዚያ በታች ውጤት መጠበቅ አለበት ማለት ነው።

ምርጥ ምስል
ሒሳብ


የባይጣጎረስ እርጉጥ ሁለት ርዝመቶችን በመቀጣጠል መደመር እንደሚቻል ሁሉ፣ ሁለት ስፋቶችን በሦሥት ጎን በማስቀመጥ እንዴት መደመር እንደሚቻል ያሳያል።


የሒሳብ ቅርንጫፎች


አጠቃላይ መሰረቶች ቁጥር ኅልዮት
ሒሳብ
ሒሳብ
ሒሳብ
ሥነ-ጠጣር ሒሳብ ትንታኔ አልጀብራ
ሒሳብ
ሒሳብ
  • ትንታኔ
  • መደብ:አስረካቢ (ፈንክሽን)
    • አስረካቢያዊ ትንታኔ
    • ልዩ አስረካቢዎች
  • ካልኩለስ
    • መደብ:ጨረር
    • ሥነ ለውጥ እኩልዮሽ (ዲፍረንሺያል ኢኩዌዥን)
    • ውድድር ካልኩለስ (ቫሪየሽናል ኢኩዌዥን)
  • እውን ትንትኔ (ሪል አናላይሲስ)
  • ውስብስብ ትንታኔ (ኮምፕሌክስ አናላይሲስ)
  • መለኪያ ኅልዮት (ሜዠር ቲየሪ)
  • ሃርሞኒክ ኅልዮት
  • ልዩ ፈንክሽኖች
  • የካልኩለስ መሰረታዊ እርግጥ
ሒሳብ
  • አልጀብራ
  • ኢለመንታሪ አልጀብራ
  • ንጥር አልጀብራ (አብስትራክት አልጀብራ)
    • ቡድን ኅልዮት (ግሩፕ ቲየሪ)
    • ሁስሊሰብ ኅልዮት (ሪንግ ቲየሪ)
    • መስክ ኅልዮት (ፊልድ ቲየሪ)
    • ነጸብራቃዊ አልጀብራ (ኮሚታቲቭ አልጀብራ)
  • የጅዎሜትሪ አልጀብራ
  • ሊኒያር አልጀብራ
  • ሁለንተናዊ አልጀብራ (ዩኒቨርሳል አልጀብራ)
  • አሰላለፍ አልጀብራ (ኦርደር አልጀብራ)
  • የአልጀብራ መሰረታዊ እርግጥ
ጂዎሜትሪ ቶፖሎጂ ተግባራዊ ሒሳብ
ሒሳብ
  • ጂዎሜትሪ
  • ዩክሊዳዊ ጂዎሜትሪ
  • ኢ-ዩክሊዳዊ ጂዎሜትሪ
  • አፊን ጂዎሜትሪ
  • አጥሊ ጂዎሜትሪ(ፕሮጄክቲቭ ጂዎሜትሪ)
  • ሥነ ለውጥ ጂዎሜትሪ (ዲፈረንሻል ጂዎሜትሪ)
    • ራይማናዊ ጂዎሜትሪ
    • የላይ ቡድን
  • አልጀብራዊ ጂዎሜትሪ
  • ትሪጎኖሜትሪ


ሒሳብ
  • ቶፖሎጂ
    • አጠቃላይ ቶፖሎጂ
    • አልጀብራዊ ቶፖሎጂ
    • ጂዎሜትራዊ ቶፖሎጂ
ሒሳብ
  • ተግባራዊ ሒሳብ
  • ቁጥራዊ ትንታኔ
  • ሒሳባዊ ሥነ ሕይወት
  • ሥነ ልክ (ኦፕቲማይዜሽን ቲየሪ)
  • ሥነ እንቅስቃሴያዊ ኅልዮት (ዳይናሚክ ቲየሪ)
    • ኬዮስ ኅልዮት
  • የገንዘብ ሒሳብ
  • ሥነ ምስጢር(ክሪፕቶግራፊ)
  • ሒሳባዊ ፊዚክስ
    • ጥንታዊ ፊዚክስ(ክላሲካል ፊዚክስ)
  • ሥነ ኩነት(ፕሮባብሊቲ)
  • ሥነ ውህብ (እስታቲስቲክስ)
  • ስቶያስቲክ ሂደት
  • ማስሊያ ጥናት (ኦፕሬተርስ ስተዲ)


ይህን ያውቁ ኖሯል?

    =0.69314....
    = 0.78539....
    =1.64493....
    =2.71828.....

    = 0.6931471.....
    = 0.178796.....


    = 1.41421...

Tags:

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

የቃል ክፍሎችደቡብ አሜሪካሙላቱ አስታጥቄቼልሲጥሩነሽ ዲባባአልበርት አይንስታይንጎርጎርያን ካሌንዳርሞስኮጥቁርስሜናዊ አውሮፓቤተ መስቀልየዔድን ገነትውሃሞዚላ ፋየርፎክስጳውሎስ ኞኞራስ መኮንንቅዱስ ዐማኑኤልመልከ ጼዴቅድንቅ ነሽበዓሉ ግርማዘምባባየተባበሩት መንግሥታት ድርጅትደብረ ሊባኖስሎስ አንጄሌስቁርአንየአማራ ክልል መዝሙርየማርቆስ ወንጌልሜክሲኮቤተ ጎለጎታሴት (ጾታ)ፈተና፤ የዕንባ ጉዞዎች እና ሌሎች ግጥሞችጨረቃየወባ ትንኝሄሮዶቶስየኢትዮጵያ ሶማሊያ ጦርነትየኖህ ልጆችሳይንሳዊ ዘዴውሻአፄኣበራ ሞላጅማ1971 እ.ኤ.አ.እየሩሳሌም640 እ.ኤ.አ.ራያዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግቋንቋየኣማርኛ ፊደልተስፋዬ ሳህሉየልም እዣትኪዳነ ወልድ ክፍሌMode Gakuen Cocoon Towerሞንቴቪዴዮ ዋንደረረስግብረ ስጋ ግንኙነትቅልየኢትዮጵያ ሕግናምሩድኦሮሚያ ክልልየኮምፒዩተር አውታርኒው ዮርክ ከተማList of academic disciplinesአበበ ቢቂላፍቅርጋምቤላ ሕዝቦች ክልልኩኩ ሰብስቤአዋሽ ወንዝክርስትናፖልኛባሕልደርግአቡነ ባስልዮስ🡆 More