ረመዳን በሂጅራ አቆጣጠር ዘጠነኛው ወር እና በሙስሊሞች ዘንድ የጾም፣ ጸሎት ወር ነው ፡፡ ረመዳን ከአምስቱ የእስልምና ማዐዘናት ዉስጥ አንዱ ነው ። እና ሃያ ዘጠኝ ወይም ሠላሳ ቀናት ይቆያል ።
ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ ምትጠልቅ ድረስ መጾም ለአቅመ አዳም (ሄዋን) ለደረሱ ሙስሊሞች ፋርድ (ግዴታ) ነው ። የክሮኒክ በሽተኞች , መንገደኞች, አረጋውያን, ጡት አጥቢ እናቶች, የስኳር በሽተኞች, ወይም የወር አበባ ያላቸው እንስቶች ሲቅሩ ከሱቢህ ( ፈጅር) አዛን ቀደም ብሎ በለሊት(ንጋት) ላይ የሚበላው ምግብ ሱሁር, እና ምሽት ከመግሪብ አዛን ቡሃላ የሚፈታበት(ሚፈጠርበት) ምግብ ኢፍጣር ይባላል ።
የጾም መንፈሳዊ ሽልማቶች ( ሰዋብ ) በረመዳን ውስጥ እንደሚባዙ ይታመናል ፡ በዚህ መሠረት, ሙስሊሞች ከምግብ እና መጠጥ ብቻ ሳይሆን፣ ከትምባሆ ምርቶች, ከባለቤታቸው ጋር ፆታዊ ግንኙነት፣ እንዲሁም ከመጥፎ ባህሪ ይቆጠባሉ ። ይልቁንስ ሰላት እና ቁርኣን ምቅራትን ያበዛሉ ።
የተለመደው ተግባር ከንጋት እስከ ፀሐይ መጥለቅ መፆም ነው ፡፡ ከጾም በፊት የቅድመ-ጎህ ምግብ ሱሁር ሲባል፣ ጻሃይ ስትጠልቅ ጾም የሚፈታበት ምግብ ኢፍጣር ይባላል ።
ሙስሊሞች ብዙ ጊዜን በጸሎት፣ በሰላት እና በሰደቃ(ምጽዋት) እንዲሁም ስነ ምግባራቸውን ለማሻሻል በመጣር ያሳልፋሉ ። ይህም ከታች ባለው ሃዲስ "ረመዳን ሲደርስ የገነት በሮች ይከፈታሉ፣ የሲኦል (ገሃነም) በሮች ይዘጋሉ እና ሰይጣናት ይታሰራሉ ። ”
ረመዳን በአግባቡ ከተጾመና በቂ ፈሳሽ በቀን ውስጥ ማግኘት ከተቻለ፣ ጠቃሚ የጡንቻ ክምችቶች ሳይቃጠል ኪሎ መቀነስ ስለሚያስችል የጤና በረከትም ያስገኛል ።
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ረመዳን, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.