ሰው ሰራሽ እውቀት አሳቢ የሆኑ ማሽኖች እና ሶፍትዌር የሚሰሩበት እና የሚጠኑበት ዘርፍ ነው። የዘርፉ ዋና ዋና ተመራማሪዎች እና መፅሃፍት ዘርፉን ሲገልፁ አሳቢ ነገሮችን የሚሰራ እንዲሁም የሚያጠና ብለው ነው። አሳቢ ወይም አዋቂ ነገር የሚለው አገላልፅ የሚያመለክተው ስላሉበት አካባቢ ለመረዳት መቻልን እና ከዚሁ መረዳት በመነሳት (ለመኖር የሚያስችል) ተመጣጣኝ ድርጊት ለማድረግ መቻልን ነው። ይህን ስያሜ ለመጀመሪያ ጊዜ በ 1955 የተጠቀመበት ጆን ማካርቲ ዘርፉን ሲገልፅ አሳቢ ወይም አዋቂ ማሽኖችን ለመስራት የሚደረግ ሳይንስና ምህንድስና ይለዋል።
ዘርፉ ባጠቃላይ የረቀቀና እና ገና ሁሉ አቀፍ ያልሆነ (ስፔሻላይዝድ) ነው። በዘርፉ ያሉት ልዩ ልዩ የጥናትና የምርምር ክፍሎችም የተከፋፈሉና እርስ በርስ ግንኙነት የማያደርጉ ናቸው። ከክፍፍሉ ምክንያቶች ውስጥ ታሪካዊና ማህበራዊ ምክንያቶሽ ይጠቀሳሉ ማለትም የተለያዩ የጥናትና የምርምር ክፍሎች ያደጉት በተለይ ዘርፉን በመሰረቱ ድርጅቶችና በግለሰቦች ጥረት መሆኑ ናቸው።
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ሠው ሰራሽ ዕውቀት, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.