ማንችስተር ዩናይትድ የእግር ኳስ ቡድን ሲሆን በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውስጥ ዋና ተካፋይ ነው። የሚጫወተው በራሱ ሜዳ ኦልድ ትራፎርድ ውስጥ ነው። ክለቡ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 20 የሊግ ዋንጫዎችን በማንሳት ሪከርድ ያለው ሲሆን 12 ጊዜ የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫ በማንሳትም ታሪክ ያለው ክለብ ነው። በሀብት እና በደጋፊ ብዛት ታላላቅ ከሆኑት የአለማችን ውጤታማ ክለቦች ቀዳሚው ነው። ይህ ቡድን በቅጽል ስሙ ቀያይ ሰይጣኖች ወይም በእንግሊዝኛው The Red Devils በመባል ይታወቃል። ክለቡ የተመሰረተው በ.አ.አ. 1878 Newton Heath LYR F.C. በሚባለው የመጀመሪያ መጠሪያው ነበር። ከዚያም የሀገሪቱን ሊግ የተቀላቀለው እ.አ.አ. በ1892 ነበር. ከ1938 እ.አ.አ. ጀምሮ የሀገሪቱ ዋና የእግር ኳስ ክፍል መጫወት (ከእ.አ.አ. 1974-75 አመት በስተቀር) ጀመረ። የአውሮፓን ዋንጫ በእ.አ.አ. 1968 በማሸነፍ እና የሶስትዮሽ ዋንጫን እ.አ.አ. በ1999 በማሳካት የመጀመሪያው የእንግሊዝ ክለብ ነው። እ.አ.አ. በኖቬምበር 6፣ 1986 የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ይባላሉ።
ማንችስተር ዩናይትድ | ||||
| ||||
ሙሉ ስም | ማንችስተር ዩናይትድ የእግር ኳስ ክለብ | |||
ቅጽል ስም(ሞች) | ቀያይ ሰይጣኖች | |||
ምሥረታ | 1878 እ.ኤ.አ. | |||
ስታዲየም | ኦልድ ትራፎርድ | |||
ባለቤት ሊቀመንበሮች ዋና አሰልጣኝ (አስተዳዳሪ) | ማልኮም ግሌዘር ጆል ግሌዘር እና አቭራም ግሌዘር [[ኤሪክ ቴን ሀግ ]] | |||
ሊግ | የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ | |||
ድረ ገጽ | ይፋ ድረ ገጽ (እንግሊዝኛ) | |||
|
1. ኦናና 2. ቪክቶር ሊንድሎፍ 3. ኤሪክ ቤይ4. አምራባት5. ሀሪ ማጓየር6. ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ 7. ክርስቲያኖ ሮናልዶ 8. ብሩኖ ፈርናንዴዝ 9. አንቶኒ ማርሲያል10. ማርከስ ራሽፎርድ11. ሆሉንድ12. ታይለር ማላሲያ 14. ክርስትያን ኤሪክሰን 16. አማድ ዲያሎ 17. ፍሬድ19. ራፍየል ቫራን 20. ዲያጎ ዳሎት 22. ቶም ሂተን 23 ሉክ ሻዉ 25 ሳንቾ 28. ፉካዶ ፔለስትሪ 29. አሮን ዋን ቢሳካ 33. ብራንደን ዊሊያምስ 34 ዶኒ ቫንደቢክ 36 አንቶኒ ኢላንጋ 37. ጀምስ ጋርነር38. አክሰል ተዋንዜቤ 39 ስኮት ማክቶሚናይ 43. ቴደን ሜንጊ 44. ታሂቲ ቾንግ 46. ሀኒባል መጅብሪ 49. አሊሀንድሮ ጋርናቾ 50. ሜሰን ግሪንዉድ 51. ሜሰን ማዉንት 52. ማይኖ
MAN.U FOREVER
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ማንችስተር ዩናይትድ, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.