ማሊ

የማሊ ሪፐብሊክ (ማሊ) በምዕራብ አፍሪካ የምትገኝ ወደብ የለሽ ሀገር ናት። ከምዕራብ አፍሪካ ሀገሮች በስፋት ሁለተኛ ናት። ከአልጄሪያ፣ ኒጄር፣ ቡርኪና ፋሶ፣ አይቮሪ ኮስት፣ ጊኔ፣ ሴኔጋል እና ሞሪታኒያ ጋር ድንበር ትዋሰናለች።

የማሊ ሪፐብሊክ
République du Mali

የማሊ ሰንደቅ ዓላማ የማሊ አርማ
ሰንደቅ ዓላማ አርማ
ብሔራዊ መዝሙር ማሊ
Le Mali
የማሊመገኛ
የማሊመገኛ
ማሊ በቀይ ቀለም
ዋና ከተማ ባማኮ
ብሔራዊ ቋንቋዎች ፈረንሳይኛ
መንግሥት

ፕሬዝዳንት

ምክትል ፕሬዝዳንት
ፕሬዝዳንታዊ-ሪፐብሊክ
ኢብራሂም ቡባካር ከይታ
አብዱላዬ ኢድሪሣ ማይጋ
ዋና ቀናት
ግንቦት ፳፭ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ.ም.
(ጁን 20, 1960 እ.ኤ.አ.)
 
ነፃነት ከፈረንሳይ
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
ውሀ (%)
 
1,240,192 (24ኛ)
1.6
የሕዝብ ብዛት
የ2007 ግምት
 
11,995,402 (73ኛ)
ገንዘብ ፍራንክ
ሰዓት ክልል UTC +0
የስልክ መግቢያ 223
ከፍተኛ ደረጃ ከባቢ .ml

ታሪክ

ማንዴ ሕዝቦች አውራጃውን ሠፍረው ተከታታይ መንግሥታት አጸኑ። እነዚህም የጋና መንግሥት፣ የማሊ መንግሥትና የሶንግሃይ መንግሥት ያጠቅልላሉ። በነዚህ መንግሥታት ውስጥ ቲምቡክቱ ለትምርትና ለመገበያየት ቁልፍ ከተማ ነበረች። በ1583 ዓ.ም. በሞሮኮ በተካሄደ ወረራ የሶንግሃይ መንግሥት ኃይል ለማነስ ጀመር።

ማሊ በ1880 እ.ኤ.አ. በፈረንሣይ ቅኝ ተገዝታ «ፈረንሳያዊ ሱዳን» ወይም «የሱዳን ሪፐብሊክ» ትባል ነበር።

ፈረንሳያዊ ሱዳን በኅዳር 16 ቀን 1951 ዓ.ም. በፈረንሳያዊ ማሕበረሠብ ውስጥ 'ራስ-ገዥ ሁኔታ' አገኝታ በመጋቢት 26 1951 ዓ.ም. ከሴኔጋል ጋር አንድላይ የማሊ ፌደሬሽን ሆኑ። ይህ የማሊ ፌዴሬሽን በሰኔ 13 ቀን 1952 ነጻነት አገኘ። ነገር ግን በነሐሴ 14 ቀን ሴኔጋል ከፌዴሬሽኑ ወጣች። በመስከረም 12 ቀን 1953 ዓ.ም. ፈረንሳያዊ ሱዳን በሞዲቦ ኪየታ ስር ራሷን 'የማሊ ሬፑብሊክ' አዋጀችና ከማሕበረሰቡ ወጣች።

ሞዲቦ ኪየታ በ1968 እ.ኤ.ኣ. በተደረገው መፈንቅለ መንግሥት ከወረደ በኋላ እስከ 1991 እ.ኤ.አ. ድረስ ማሊ በማውሳ ትራዎሬ ተመራች። በ1991 እ.ኤ.አ. የተካሄዱ ተቃውሞች ወደ መፈንቅለ-መንግሥት አመሩ። ከዚያም የተሸጋጋሪ መንግሥት ተቋቋመና አዲስ ሥነ-መንግሥት ተጻፈ። በ1992 እ.ኤ.አ. አልፋ ዑመር ኮናሬ የማሊን የመጀመሪያ ዴሞክራሲያዊ ምርጫን አሸነፉ።

መልከዓ-ምድር

ማሊ ከባሕር ጋር ግንኙነት የላትም። የሀገሩ አብዛኛው ክፍል በሰሐራ በረሃ ውስጥ ይገኛል። ከተፈጥሮ ሀብቶች ውስጥ ወርቅ፣ ዩራኒየም፣ ፎስፌት፣ ካዎሊን፣ ጨው፣ ኖራ (ላይምስቶን) ይጠቀሳሉ።

ፖለቲካ

የማሊ ፓርላማ 147 ሰዎች ሲኖረው እነዚህ ተወካዮች በህዝብ ብዛት ነው የሚመረጡት።

አስተዳደራዊ ክልልሎች

ማሊ በስምንት ክፍለ-ሀገሮችና አንድ ከተማ ተከፋፍላለች።

ኢኮኖሚ

ማሊ ከዓለም ደሀ ሀገሮች አንዷ ስትሆን 65 ከመቶ የሚሆነው መሬት በረሃ ነው። አብዛኛው የኤኮኖሚ እንቅስቃሴ በኒጅር ወንዝ አካባቢ ነው የሚካሄደው። 10 ከመቶ የሚሆነው ሕዝብ ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሰ የሚኖር ሲሆን 80 ከመቶ የሚሆነው የሥራ ሃይል በእርሻና ዓሣ ማጥመድ ተሰማርቷል። የኢንዱስትሪው እንቅስቃሴ በእርሻ ምርቶች ላይ ያተኩራል። የሸክላ ሥራ በሴቶች የሚከናወን ሲሆን በነጋዴዎች በገበያዎች ይሸጣል። ሸክላዎቹ የሚሰሩበት ባሕላዊ ሂደት የቱሪስት መሳቢያ ነው።

ማሊ 
በ"Wiki Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለ ማሊ የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።


Tags:

ማሊ ታሪክማሊ መልከዓ-ምድርማሊ ፖለቲካማሊ አስተዳደራዊ ክልልሎችማሊ ኢኮኖሚማሊምዕራብ አፍሪካሞሪታኒያሴኔጋልቡርኪና ፋሶኒጄርአልጄሪያአይቮሪ ኮስትአፍሪካጊኔ

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

ዮሐንስ ፬ኛማሪኦፍቅር እስከ መቃብርቬት ናምጋሞEእግር ኳስመብረቅራስ ጎበና ዳጨ ከ1882-1889የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንየአክሱም ሐውልትዶናልድ ጆን ትራምፕቴሌቪዥንሊጋባፈሊጣዊ አነጋገር አአቡነ ሰላማአቡነ ጴጥሮስጨረቃማንችስተር ዩናይትድአበበ ቢቂላፈንገስፈሊጣዊ አነጋገርየሌት ወፍአቡጊዳመጋቢትምጣኔ ሀብትረመዳንአውሮፓመንግሥተ አክሱምአፍሮ እስያዊ ቋንቋዎችናይትሮጅንቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴመሐመድደቡብ ሱዳንዋናው ገጽ/ለጀማሪወች/ፊደል አጻጻፍበሶብላትምህርተ፡ጤናግንድ የዋጠየሚጣፍጥ ምግብ ምንድን ነው ቢሉት ሲርብ የበሉት ነውዘመነ መሳፍንትየመጀመሪያው የዓለም ጦርነትደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልልራያኢትዮጲያአፋር (ክልል)አዲስ ዘመን (ጋዜጣ)እጨጌአልባኒያጌዴኦዓረብኛማሲንቆሰለሞናዊው ሥርወ መንግሥትሀይቅሸለምጥማጥክፍያጓጉንቸርአንታርክቲካሽፈራውጋሞጐፋ ዞንደቡብ አሜሪካሥነ ቅርስማህተማ ጋንዲብሔርተኝነትአዳም ረታማላዊሊዮናርዶ ዳቬንቺየኮርያ ጦርነትፍሬው ኃይሉሶማሌ ክልልዓረፍተ-ነገርቃል (የቋንቋ አካል)ሥነ ጽሑፍግዕዝልዩ ትምህርትዳኛቸው ወርቁ🡆 More