መስተፃምር -በማሰሪያ አንቀፅ ላይ እየተጫነ የአንቀፁን ማሰሪያነት የሚያስቀርና ፣ የሚመስሉ ነገሮችን የሚያጫፍር ቃል መስተፃምር ይባላል። ትርጓሜውም፣ የሚያያይዝ፣ ወይም አያያዥ ማለት ነው። በብዙ ቁጥር ሲሆን መስተፃምራን ወይም መስተፃምሮች ይባላል።
ምሳሌ :- "ያዕቆብና ዮሐንስ ትምህርትን ስለወደዱ ወደ ትምህርት ቤት እየሮጡ ይሄዳሉ።" - እነሆ በዚህ አረፍተ ነገር ውስት ሶሥት መስተፃምራን አሉ። እነርሱም "ና ፣ ስለ ፣ እየ" ናቸው። "ና" የሚለው ቃል "ያዕቆብ" እና "ዮሐንስ" በሚሉት ስም መካከል ገብቶ ሁለቱን ስሞች አያይዟል። "ስለ" የሚለው ቃል ደግሞ "ወደዱ" በሚለው ግስ ላይ ተጭኖ የአንቀፁንም ማሰሪያነት... ማሰሪያ ዓንቀጽ ላይ እየተጫነ የአንቀፁን ማሰሪያነት የሚያስቀርና ስሞችን የሚያጫፍር ቃል ሁሉ "መስተፃምር" ይባላል።
ምንጭ ያማርኛ ሰዋስው ፣ ብላታ መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article መስተፃምር, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.