መለጋሲ (Malagasy) ከአውስትሮኔዚያን የቋንቋ ቤተሠብ ቋንቋዎች ሁሉ ምእራበኛው ሲሆን የማዳጋስካር መደበኛ ቋንቋ ነው። 1500-2000 አመታት ከዛሬ በፊት ከእንዶኔዚያ የመጡ የማዳጋስካር ኗሪዎች ቋንቋ በመሆኑ፣ ከቃላቱ መዝገብ 90% ከመቶ በቦርኔዮ እንዶኔዚያ ከተገኘው ቋንቋ ከማአንያን ጋራ ተመሳሳይ ነው። የቀሩትም 10% ቃላት በተለይ ከአፍሪቃ ቋንቋዎች (ከባንቱ) እና ከአረብኛ ተበድረዋል።
በአረፍተ ነገር ውስጥ ግሡ ከሁሉ ይቀድማል። ይህ ተራ እንደ ዕብራይስጥ ይመስላል እንጂ ለብዙዎች ቋንቋዎች የተለመደ አይደለም። በየቃሉ ውስጥ ከመጨረሻው ክፍለ-ቃል በፊት የሆነው ክፍለ-ቃል አናባቢ ይጠበቃል፤ ሌሎቹ አናባቢዎችም ይነበነባሉ (በሙሉ አይስሙም)፤ ስለዚህ "Malagasy" እንደ ፈረንሳይኛ አጻጻፉ "Malgache" (መልጋሽ) ይመስላል።
ነገር ግን መጨረሻው ክፍለ-ቃል -ka (-ከ), -tra (-ትረ), ወይም -na (-ነ) ሲሆን፣ የተጠበቀው ከመጨረሻው 2 በፊት የሆነው ክፍለ-ቃል ነው። በዚህ መንገድ "fanorona" የሚለው ቃል እንደ "ፈኑርን" ይመስላል። (በአጻጻፍ ረገድ፣ "o" የሚለው ፊደል እንደ "ኡ" ይመስላል፤ "-i" በመጨረሻ ሲሆን "-y" ይሆናል።)
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article መለጋሲ, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.